إعدادات العرض
ደረጃ ያላቸው ስራዎች
ደረጃ ያላቸው ስራዎች
1- ‹ባሏ ለሞተባትና ለሚስኪን የሚለፋ ሰው ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ሰው አምሳያ ወይም ልክ ሌሊት እየሰገደ ቀኑን እንደሚፆም አምሳያ ነው›
2- ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ! ቀብሬንም የሚጎበኝ የበአል ስፍራ አታድርጉት! ይልቅ በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ! የትም ብትሆኑ ሶለዋታችሁ ትደርሰኛለችና።
3- ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።
5- ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው።
7- አንድ ባሪያ አንድን ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!
10- ሲሳዩ እንዲሰፋለትና እድሜው እንዲረዝምለት የወደደ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል።
11- 'ዱዓእ እሱ አምልኮ ነው።
12- ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።
14- አስር ጊዜ 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር' ያለ ሰው
15- አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል።
16- 'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።)
18- አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ ሊገዙትና በሱ ላይም አንዳችንም ላያጋሩ ሲሆን፤ ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ ደግሞ በሱ ላይ አንዳችንም ያላጋራን ላይቀጣ ነው።
19- በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት ገባ፤ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።" አሉ።
20- የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች ከኔ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው ይመርጣል
22- 'አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜ አንዳችሁ ከልቡ 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤
23- ከፍ ያለው አላህ እንዲህ አለ: 'ሶላትን በኔና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፈልኩት። ለባሪያዬም የጠየቀው አለው።
24- ጠርጥሬያችሁ አይደለም ያስማልኳችሁ። ነገር ግን ጂብሪል መጥቶ አላህ በናንተ መላእክትን እንደሚፎካከር ስለነገረኝ ነው።› አሉ።
26- ሁለት ሴት ልጆችን እስኪደርሱ ድረስ የተንከባከበ ሰው የትንሳኤ ቀን እኔና እሱ እንዲህ ሆነን ይመጣል።" ጣታቸውንም አጣበቁ።
30- በአላህ እምላለሁ! ለአንተ ቀይ ግመል ከሚኖርህ በአንተ ሰበብ አላህ አንድ ሰው ቢመራልህ የተሻለ ነው።
31- ጌታችሁን አላህ ፍሩ፣ አምስት (አውቃት) ሶላታችሁን ስገዱ ፣ የፆም ወራችሁን ፁሙ፣ የገንዘባችሁንም ዘካ ስጡ፣ መሪያችሁን ታዘዙ፤ የጌታችሁን ጀነት ትገባላችሁ።
32- አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?
33- በላጩን ሥራችሁ፣ ንጉሳችሁ ዘንድ የጠራችውን ሥራችሁ፣ ደረጃችሁንም ከፍ የምታደርገውን ስራችሁን፣
35- ሙፈሪዶች ቀደሙ!
37- እንዳልከው ከሆነ አንተ ትኩስ አመድ እያቃምካቸው ነው። በዚህ ሁኔታ ላይ እስከዘወተርክ ድረስም ከአላህ የሆነ አጋዥ ከአንተ ጋር አይወገድም።" አሉት።
39- ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።
40- እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።
41- ቁርአንን አሳምሮ የሚያነብ ሰው የተከበሩና ታዛዥ ከሆኑ መላዕክቶች ጋር ነው፤ ቁርኣንን ሲያነብ ከብዶት እየተቸገረ የሚያነብ ሰው ደሞ ለርሱ ሁለት ምንዳ አለው።
47- ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።
48- ዕውቀትን ዑለሞችን ልትፎካከሩበት (በሊቃውንት ፊት ለመታየት)፣ ቂሎችን ልትሟገቱበት
50- አንዳችሁ ወደ ቤተሰቡ የተመለሰ ጊዜ ሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎችን ቢያገኝ ያስደስተዋልን?
52- ቁርኣንን ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነብ ምፅዋትን በይፋ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው፤ ቁርኣንን በዝግታ የሚያነብ ምፅዋትን በድብቅ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው።
55- ላ ኢላሀ ኢለላህ በል የትንሳኤ ቀን ላንተ በርሱ እመሰክርልሀለሁ
56- አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ።
57- ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!
58- አላህ ለርሱ ፊት ብቻ ተብሎና ጥርት ተደርጎ የተሰራ ስራን ካልሆነ በቀር አይቀበልም።" አሉ።
72- ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል።