إعدادات العرض
ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!
ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!
ከዑሥማን ቢን አቢል ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰይጣን በኔና በሶላቴ እንዲሁም በቂረአቴ መካከል አዘናጋኝና በኔ ላይ ያለባብስብኛል።" አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!" አሉት። እርሱም "ይህንን ፈፀምኩ አላህም አስወገደልኝ።" አለ።
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kiswahili ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली తెలుగు Bosanski ಕನ್ನಡ Kurdî മലയാളം Oromoo Română Italiano Soomaali Shqip Српски Українська Wolof Moore Tagalog Malagasy தமிழ் Azərbaycan فارسی ქართული 中文 Magyarالشرح
ዑሥማን ቢን አቢልዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰይጣን በኔና በሶላቴ መካከል ጋሬጣ ሆነ በርሷ ውስጥ ከመመሰጥም ከለከለኝ። በኔ ላይ ሶላቴ ውስጥ የምቀራውን ቂረአቴን ቀላቀለብኝም አጠራጠረኝም።" የአላህ መልዕክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉት: "ይህ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህንን ያገኘህና የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ። ወደ ግራህም ዞረህ ከትንሽ ምራቅ ጋር ሶስት ጊዜ ትፋ።" ዑሥማንም እንዲህ አለ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያዘዙኝን ነገር ፈፀምኩ። አላህም ከኔ ላይ አስወገደልኝ።"فوائد الحديث
ሶላት ውስጥ መመሰጥና ልብን መጣድ አንገብጋቢ መሆኑን እንረዳለን። ሰይጣንም ሶላት ውስጥ በመወስወስና በመጎትጎት ይታገላል።
ሰይጣን ሶላት ውስጥ በሚወሰውስ ወቅት ወደ ግራ ከመትፋት ጋር ሶስት ጊዜ "አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧኒ አርረጂም" ሶስት ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በሚያጋጥማቸው ችግሮች ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ችግራቸውን እስኪፈቱላቸው ድረስ ወደርሳቸው እንደሚመለሱ መገለፁን እንረዳለን።
የሶሐቦች ልብ ህያው መሆኑን እንረዳለን። ሀሳባቸው ሁሉ መጪው አለም ነው።