إعدادات العرض
አንድ ባሪያ አንድን ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!
አንድ ባሪያ አንድን ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከላቀውና ከተከበረው ጌታቸው ባስተላለፉት (ሐዲሥ) እንዲህ አሉ "አንድ ባሪያ አንድን ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ! " የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም አሁንም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ! የፈለግከውን ስራ በርግጥ ላንተ ምሬሃለሁ።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල தமிழ் ไทย دری Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски O‘zbek Moore नेपाली Malagasy тоҷикӣ Oromoo Wolof Soomaali Български Українська Azərbaycan ქართული bm Lingala Македонскиالشرح
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጌታቸው በሚያወሩት ሐዲሥ አንድ ባሪያ አንድ ወንጀል ሰርቶ ከዚያም "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" ካለ አላህ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀሉን የሚምረው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ብሎ ይሸሽገዋልም ከሱ ይቅር ይለዋልም። ወይም ምሬዋለሁ የሚል ንግግር እንደሚያስከትልለት ነገሩን። ከዚያም ባሪያው በድጋሚ ወንጀል ይሰራና "ጌታዬ ወንጀሌን ማረኝ!" ይላል። አላህም "ባሪያዬ ወንጀልን ሰራ። ለሱ ወንጀልን የሚምር ጌታ እንዳለው አወቀ።" ይልና ይሸሽገዋልም ከሱ ይቅር ይለዋልም። ወይም የሚቀጣውን ቀጥቶ "ለባሪያዬ ምሬዋለሁ" ይላል። ከዚያም ባሪያው በድጋሚ ወንጀል ይሰራና "ጌታዬ ወንጀሌን ማረኝ!" ይላል። አላህም "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምር ጌታ እንዳለው አወቀ!" ይልና ይሸሽገዋልም ከሱ ይቅር ይለዋልም። ወይም የሚቀጣውን ቀጥቶ "ለባሪያዬ ምሬዋለሁ" ይላል። አላህ እንዲህም ይላል: ወንጀልን በሰራ ቁጥር ወንጀሉን በመተውና በመፀፀት ዳግም ወደ ወንጀል ላለመመለስም ቆርጦ እየወሰነ ነገር ግን ነፍሱ እያሸነፈችው ወንጀል ላይ በድጋሚ እየወደቀ በዚህ መልኩ ወንጀል ቢሰራም ተውበት ማድረግን እስካዘወተረ ድረስ የሰራውን ቢሰራ እምረዋለሁ። ተውበት ያለፈውን ወንጀል ታብሳለችና።فوائد الحديث
አላህ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ስፋቱን ፤ የሰው ልጅ ምንም ያክል ወንጀል ቢሰራ ወደ አላህ ተውበት ካደረገና ከተመለሰ አላህ ተውበቱን እንደሚቀበለው፤
በአላህ ያመነ የጌታውን ይቅርታ ተስፋ ያደርጋል፣ ቁጣውንም ይፈራል፣ ወደ ተውበት ይቻኮላል እንጂ በወንጀል ላይ አይቀጥልም።
የትክክለኛ ተውበት መስፈርቶች: ከወንጀል መውጣት፣ በወንጀሉም መፀፀት፣ ዳግም ወደ ወንጀል ላለመመለስ መቁረጥ ነው። ተውበት የሚያደርገው ባሮችን በገንዘብ ወይ በክብር ወይ በነፍስ ከመበደል ወንጀል ከሆነ አራተኛ መስፈርት ይጨመራል። እሱም: ተበዳዩ ባለመብት ሀላል እንዲያደርግለት (ዓውፍ እንዲለው) መጠየቅ ወይም ሓቁን መስጠት ነው።
አንድን ባሪያ ስለዲኑ ጉዳይ አዋቂ የሚያደርገው የሆነውን አላህን ማወቅ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ተረድተናል። ስለአላህ ማወቁ ወንጀል በሰራ ቁጥር ተስፋ ሳይቆርጥና ወንጀሉ ላይ ሳይዘልቅ እንዲቶብት ያደርገዋልና።
التصنيفات
የዚክር ትሩፋቶች