አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል።

አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል።

ከሙዓዊያህ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ፦ "አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል። እኔ አከፋፋይ ብቻ ነኝ አላህ ነው የሚሰጠው። ይህች ኡማህ በአላህ ትእዛዝ ላይ የቆመች ከመሆን አትወገድም! የአላህ ትእዛዝ እስክትመጣ ድረስም የተቃረናቸው ሁሉ አይጎዳቸውም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ሃይማኖቱን መገንዘብ እንደሚቸረው፤ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ ከሰጣቸው ሲሳይ፣ ዕውቀትና ሌሎችም ነገሮች የሚያከፋፍሉና የሚያሰራጩ አከፋፋይ ብቻ እንጂ ትክክለኛው ሰጪ አላህ ብቻ ነው። ከሱ ውጪ ያሉት ከሰበብነት የዘለለ ከርሱ ፈቃድ ውጪ እንደማይጠቅሙ፤ ይህ ኡማህ በአላህ ትእዛዝ ላይ ከመቆም እንደማይወገድና ትንሳኤ እስከሚቆም ድረስም የተፃረራቸው እንደማይጎዳቸው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።

فوائد الحديث

ሸሪዐዊ ዕውቀት እና እርሱን መማር ያለው ትሩፋት ትልቅ መሆኑንና በርሱም ላይ መነሳሳቱን ተረድተናል፤

በእዚህ ኡማህ ውስጥ በእውነት ላይ የሚቆም መኖሩ የማይቀር ጉዳይ መሆኑን፤ ከእውነተኛ መንገድ አንዱ ሲገለል ሌላው በእውነት ላይ ይቆማል።

ሃይማኖትን መገንዘብ አላህ ለባሪያው መልካም ከመሻቱ የሚመደብ መሆኑን ፤

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚሰጡት በአላህ ትእዛዝና ፍላጎት ብቻ መሆኑንና ያለርሱ ፈቃድ አንድም ነገር ማድረግ እንደማይችሉ ተረድተናል።

التصنيفات

የእውቀት ትሩፋት