إعدادات العرض
አንድ ሙስሊም ሰው ለወንድሙ ከሩቅ (በሌለበት) የሚያደርግለት ዱዓ ተቀባይነት አለው።
አንድ ሙስሊም ሰው ለወንድሙ ከሩቅ (በሌለበት) የሚያደርግለት ዱዓ ተቀባይነት አለው።
ከኡሙ ደርዳ እና ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ይሉ ነበር: «አንድ ሙስሊም ሰው ለወንድሙ ከሩቅ (በሌለበት) የሚያደርግለት ዱዓ ተቀባይነት አለው። ከጭንቅላቱ በላይ የተወከለ መልአክ አለ። ለወንድሙ መልካም ነገርን ዱዓ ባደረገለት ቁጥር ለዚህ ጉዳይ የተወከለው መልአክም "አሚን ላንተም ተመሳሳዩ አለህ።" ይለዋል።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Hausa Kurdî தமிழ் Magyar ქართული Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Português मराठी ភាសាខ្មែរ دریالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙስሊም የሆነ ሰው ለሙስሊም ወንድሙ ከሩቅ ‐ ዱዓ የሚደረግለት ሰው በሌለበት ‐ የሚያደርገው ዱዓ ተቀባይነት እንዳለው ተናገሩ። ይህም የኢኽላስ ጥግ የደረሰ ዱዓ ስለሆነ ነው። ዱዓ አድራጊው ጭንቅላት ዘንድም የተወከለ መልአክ እንዳለና ለወንድሙ መልካም ነገርን ዱዓ ባደረገ ቁጥር ለዚህ ጉዳይ የተወከለው መልአክ "አሚን ላንተም ዱዓ ያደረግከውን አምሳያ ይስጥህ።" እንደሚልም ተናገሩ።فوائد الحديث
አማኞች በዱዓ እንኳን ቢሆን እርስ በርሳቸው መልካም እንዲዋዋሉ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ከሩቅ ዱዓ ማድረግ እውነተኛ ኢማንና ወንድማማችነት እንዳለ ፍንትው አድርጎ ያሳያል።
ዱዓ ማድረግን ከሩቅ በሚለው መገደቡ ጥግ ለደረሰ ኢኽላስና ተመስጦ ምቹ ስለሆነ ነው።
ዱዓ ተቀባይነት ከሚያገኝባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ አንድ ሙስሊም ለወንድሙ ከሩቅ ዱዓ ማድረጉ ነው።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከሩቅ በሌለበት ለሙስሊም ወንድም ዱዓ ማድረግ ያለውን ደረጃ እንረዳለን። ዱዓውን ያደረገው ለበርካታ የሙስሊም ጀመዓዎች ቢሆንም ይህን ደረጃ ያገኛል። ለሙስሊሞች ባጠቃላይም ቢያደርግም የሐዲሡ ግልፅ መልዕክት እንደሚያሳየው አሁንም ይህን ደረጃ ያገኛል። አንዳንድ ቀደምቶች ለራሳቸው ዱዓ ማድረግ በሚፈልጉበት ወቅት ዱዓቸው ተቀባይነት እንዲያገኝና የዱዓውን ተመሳሳዩን ስለሚያስገኝላቸው ያቺን ለራሳቸው የፈለጓትን ነገር ለሙስሊም ወንድማቸው ዱዓ ያደርጉ ነበር።"
አንዱ የመልአኮች ተግባር ተገልጿል። ከመልአኮች መካከል አላህ ለዚህ ሥራ የወከለው አለ።