'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።)

'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።)

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።) (ይሄንን ስል) {አሊፍ ላም ሚም} አንድ ፊደል ነው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን {አሊፍ} አንድ ፊደል ነው። {ላም} አንድ ፊደል ነው። {ሚም} አንድ ፊደል ነው።'"

[ሐሰን ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ማንኛውም ከአላህ መጽሐፍ አንድ ፊደል የሚቀራ ሙስሊም ለርሱ ምንዳ እንዳለውና አንዱ ምንዳ ደግሞ ለርሱ በአምሳያው እስከ አስር ድረስ እንደሚባዛለት ተናገሩ። ከዚያም ይህንን ({አሊፍ ላም ሚም} አንድ ፊደል ነው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን {አሊፍ} አንድ ፊደል ነው። {ላም} አንድ ፊደል ነው። {ሚም} አንድ ፊደል ነው።) በሚለው ንግግራቸው ሶስት ፊደል እንደሚሆኑና ሰላሳ ምንዳ እንደሚሆኑ ገለፁ።

فوائد الحديث

ቁርአን ማንበብ በማብዛት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

አንድ ቁርአን አንባቢ የሚያነባቸው ሁሉም ቃላት ውስጥ የሚገኙ ፊደላት በአስር አምሳያቸው የሚባዙ የሆኑ ምንዳዎች አሉት።

አላህ ለባሮቹ በራሱ ቸርነት ምንዳዎችን ማባዛቱ የርሱ እዝነትና ቸርነት ሰፊ መሆኑን ያስረዳናል።

ቁርአን ከሌሎች ንግግሮች በላይ ያለውን ብልጫና ማንበቡም አላህን ማምለኪያ መሆኑን እንረዳለን። ይህም እርሱ የአላህ ቃል ስለሆነ ነው።

التصنيفات

ለቁርአን ትኩረት የመስጠት ትሩፋት, የተከበረው ቁርአን ትሩፋቶች