إعدادات العرض
1- ይህንን ቁርአን ተጠባበቁት! የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ እርሱ (ቁርአን) ግመል ከታሰረችበት (ፈታ) ከምታመልጠው የበለጠ በጣም የሚያመልጥ ነው።
2- ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።
3- 'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።)
4- ቁርኣንን የሚቀራ ሙእሚን ምሳሌው እንደ ትርንጎ ነው። ሽታዋም ምርጥ ነው። ጣዕሟም ምርጥ ነው። ቁርአንን የማይቀራ ሙእሚን ምሳሌው እንደ ተምር ነው። ሽታ የላትም ጣዕሟ ግን ጣፋጭ ነው።
5- ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል።