إعدادات العرض
ይህንን ቁርአን ተጠባበቁት! የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ እርሱ (ቁርአን) ግመል ከታሰረችበት (ፈታ) ከምታመልጠው የበለጠ በጣም የሚያመልጥ ነው።
ይህንን ቁርአን ተጠባበቁት! የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ እርሱ (ቁርአን) ግመል ከታሰረችበት (ፈታ) ከምታመልጠው የበለጠ በጣም የሚያመልጥ ነው።
ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ይህንን ቁርአን ተጠባበቁት! የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ እርሱ (ቁርአን) ግመል ከታሰረችበት (ፈታ) ከምታመልጠው የበለጠ በጣም የሚያመልጥ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili မြန်မာ ไทย Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල தமிழ் دری Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Română Kinyarwanda नेपाली Српски Wolof Soomaali Moore Українська Български Azərbaycan mr ქართული тоҷикӣ bm Oromoo Македонскиالشرح
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ሰው ቁርአንን በልቡ ከሸመደደው በኋላ እንዳይረሳው ቁርአንን በመጠባበቅና በማንበቡ ላይ መዘውተርን አዘዙ። ቁርአን ከልብ ውስጥ ከታሰረች ግመል የበለጠ እጅግ የሚጠፋና የሚወገድ መሆኑን ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመሀላቸው በማጠናከር ገለፁ። ግመል በክንዶቿ መሀል በገመድ ተጠፍራ ስታበቃ ሰውዬው ከተጠባበቃት ይይዛታል፤ ከለቀቃት ግን ትሄዳለችም ትጠፋለችም።فوائد الحديث
ቁርአንን የሸመደደ ሰውም ቁርአንን በማንበቡ ላይ በየጊዜው ከዘወተረ ልቡ ውስጥ እንደተጠበቀ ይቀራል። ያለበለዚያ ግን ይጠፋበታልም ይረሳዋልም።
ቁርአንን ከመጠባበቅ ጥቅሞች መካከል ምንዳና አጅርን ማግኘትና የትንሳኤ ቀን ከፍተኛ ደረጃን መጎናፀፍ ነው።
التصنيفات
ለቁርአን ትኩረት የመስጠት ትሩፋት