ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" …

ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል።

ዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ለቁርኣን ባለቤት "አንብብ! (ደረጃን) ውጣ! በዱንያ ውስጥ አሳምረህ ታነብ እንደነበርከው አሳምረህ አንብብ! (ጀነት ውስጥ) ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል።"

[ሐሰን ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ቁርኣንን ለሚያነብ፣ ቁርኣን ውስጥ ባለው ለሚሰራ፣ በቃሉ መሸምደድንም ሆነ አሳምሮ ማንበብን አጥብቆ የያዘ ጀነት በሚገባ ጊዜ "ቁርኣንን አንብብ! በዚህም ሰበብ የጀነት ደረጃዎችን ውጣ! ቁርኣንን በስክነትና እርጋታ ዱንያ ላይ ታነበው እንደነበርከው አንብብ! ያንተ ስፍራ የምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ዘንድ ነው።" ይባላል በማለት ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ተናገሩ።

فوائد الحديث

በቁጥርም ሆነ በሁኔታ ለሥራችን በሚመጥን መልኩ ነው የምንመነዳው።

ቁርኣንን በማንበብ፣ አሳምሮ መቅራት፣ በመሸምደዱ፣ በማስተንተኑና በቁርኣን በመስራት ላይ መበረታታቱ።

ጀነት በርካታ ደረጃዎችና እርከኖች ያሏት ሲሆን የቁርኣን ባለቤት የሆነ ሰው ከፍተኛ የሆነውን ደረጃ ነው የሚያገኘው።

التصنيفات

ለቁርአን ትኩረት የመስጠት ትሩፋት, የተከበረው ቁርአን ትሩፋቶች