ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።

ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።

ከዑስማን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ከናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ሰው ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሙስሊሞች መካከል በላጩና አላህ ዘንድ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ቁርአን ማንበብን፣ መሸምደድን፣ ማሳመርን፣ መገንዘብንና ማብራራትን የተማረና እርሱ ዘንድ ያለውን የቁርአን እውቀት ከመተግበሩም ጋር ለሌላው ያስተማረ መሆኑን ተናገሩ።

فوائد الحديث

የቁርአን ልቅና መገለፁ። ቁርአን የአላህ ቃል ስለሆነ ምርጡ ቃል ነው።

ምርጥ ተማሪ ማለት ሌላውንም የሚያስተምር እንጂ በነፍሱ ላይ የሚገደብ አይደለም።

ቁርአንን መማርና ማስተማሩ ማንበቡንም፣ ትርጉሙንም ህግጋቱንም ያካትታል።

التصنيفات

ለቁርአን ትኩረት የመስጠት ትሩፋት