إعدادات العرض
አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!
አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!"
الترجمة
العربية Bosanski English فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Español Hausa Kurdî Português සිංහල Kiswahili অসমীয়া Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands മലയാളം Românăالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የርሳቸውን ሐዲሥ ሰምቶ ለሌላው እስኪያደርስ ድረስ የሸመደደ ሰው አላህ በዱንያ ውስጥ ውበትን፣ ቁንጅናና ብርሃንን እንዲሰጠው፤ በመጪው አለም ደግሞ ወደ ጀነት ብርሃን፣ ፀጋና ውበት አላህ እንዲያደርሰው ዱዓ አድጉለት። አንዳንዴ ሐዲሥ የሚነገረው ሰው ሐዲሡን መጀመርያ ከሰማው ሰው የበለጠ ሸምዳጅ፣ ተገንዛቢ፣ ከሐዲሡ ፍሬሃሳቦችን መዞ የሚያወጣ ይሆናል። በዚህም የመጀመሪያው ሰውዬ በአስተማማኝ መልኩ መሸምደዱንና "ነቅል" (መውሰድን) ሲችል ሁለተኛው ደግሞ በአስተማማኝ መልኩ መገንዘቡንና መረዳቱን የቻለ ይሆናል።فوائد الحديث
የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሐዲሥ በመሸምደድና ለሰዎች በማድረስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
የሐዲሥ ምሁራኖች ያላቸው ደረጃና ሐዲሥን የመፈለግ ልቅና መገለፁ፤
የግንዛቤ ባለቤቶች የሆኑት ዑለማዎች ያላቸው ደረጃን እንረዳለን።
ሶሐቦች (ሪድዋኑሏሁ ዐለይሂም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሐዲሥን ሰምተው ለኛ ማድረሳቸው የነርሱን ደረጃ ያስረዳናል።
አልመናዊ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ሐዲሥን ለማስተላለፍ ሐዲሡን ፈቂህ (መገንዘብ) መስፈርት እንዳልሆነ ገለፆልናል። ሐዲሥ ለማስተላለፍ መስፈርቱ መሸምደድ ነው። ፈቂህ (በደንብ ተገንዛቢ) የሆነ ሰው ደግሞ ሐዲሡን መገንዘብና ማስተንተን ይገባዋል።"
ኢብኑ ዑየይናህ እንዲህ ብለዋል: "ሐዲሥን የሚፈልግ ሰው ሁሉ በዚህ ሐዲሥ መሰረት ፊቱ ላይ ብርሃን አለው።"
የሐዲሥ ሊቃውንቶች ዘንድ ሽምደዳ ሁለት አይነት ነው: እነርሱም: በቀልብ መሸምደድ እና በመጽሐፍና በጽሑፍ መጠበቅ ነው። ሁለቱንም ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰው ዱዓእ ይጠቀልላቸዋል።
የሰዎች ግንዛቤ ይበላለጣል። አንዳንድ ሐዲሥ የደረሳቸው መጀመርያ ከሰማው የበለጠ ተገንዛቢ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ፊቂህን የተሸከሙ ሆነው (ፈቂህ ያልሆኑ) ግንዛቤ የሌላቸውም ስንትና ስንት ሰዎች ይኖራሉ?!