በአላህ እምላለሁ! ለአንተ ቀይ ግመል ከሚኖርህ በአንተ ሰበብ አላህ አንድ ሰው ቢመራልህ የተሻለ ነው።

በአላህ እምላለሁ! ለአንተ ቀይ ግመል ከሚኖርህ በአንተ ሰበብ አላህ አንድ ሰው ቢመራልህ የተሻለ ነው።

ከሰህል ቢን ሰዕድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የኸይበር ቀን እንዲህ አሉ: "ነገ ይህንን ባንዲራ አላህ በርሱ እጅ ድልን ለሚያጎናፅፍ፣ አላህና መልክተኛውን ለሚወድ፣ አላህና መልክተኛውም የሚወዱት ለሆነ ሰው እሰጠዋለሁ።" ሰዎችም ለማን ነው የሚሰጠው? በሚል ሌሊታቸውን ተጠምደውበት አደሩ። ሰዎችም ያነጉ ጊዜ ሁሉም ባንዲራው እንዲሰጠው ተስፋ በማድረግ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ማልደው ሄዱ። እርሳቸውም "ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ የት አለ? አሉ። ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አይኑን አሞታል" ተባሉ። እርሳቸውም "ሰው ላኩበት!" አሏቸው። እርሱም ተይዞ መጣና የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዓይኑ ላይ ተፉና ዱዓ አደረጉለት። እርሱም ከዚህ በፊት ምንም በሽታ እንዳልነበረበት ሆኖ ተፈወሰ። ባንዲራውንም ሰጡት። ዐሊይም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንደኛው አምሳያ እስኪሆኑ ድረስ ልዋጋቸውን?" በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም አሉት: "ቀያቸው እስክትሰፍር ድረስ ተረጋግተህ ተጓዝ። ቀጥሎ ወደ እስልምና ጥራቸው። በነርሱ ላይ ግዴታ የሚሆንባቸውንም የአላህ ሐቅ ንገራቸው። በአላህ እምላለሁ! ለአንተ ቀይ ግመል ከሚኖርህ በአንተ ሰበብ አላህ አንድ ሰው ቢመራልህ የተሻለ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

በማግስቱ በኸይበር አይሁዶች ላይ ሙስሊሞች ድልን እንደሚጎናፀፉ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶሐቦች ነገሯቸው። ይህም እሳቸው ባንዲራ በሚሰጡት ሰው እጅ ነው። ይህም (ባንዲራ) ሰራዊቶች ለምልክትነት የሚይዙት አርማ ነው። ባንዲራው የሚሰጠው ሰው ባህሪም አላህና መልክተኛውን ይወዳል፣ አላህና መልክተኛውም ይወዱታል። ሶሐቦችም ይህንን ትልቅ ክብር በመፈለግ ባንዲራውን ስለሚሰጠው ሰው ማንነት ሲያወጉ ሌሊታቸውን ተጠምደውበት አደሩ። በማግስቱም ሁሉም ይህን ክብር መጎናፀፍን ተስፋ በማድረግ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሄዱ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ ዐሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ጠየቁ። አይኖቹን እንደታመመ ነገሯቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደርሱ ሰው ላኩና ይዘውት መጡ። ከተከበረው ምራቃቸውም በዐሊ አይኖች ላይ ተፉና ዱዓ አደረጉለት። ምንም በሽታ እንዳልያዘው ሰው እስኪመስል ድረስ ከበሽታው ተፈወሰ። ባንዲራውንም ሰጡትና የጠላት ምሽግ እስኪቀርብ ድረስ በእርጋታ እንዲጓዝ አዘዙት። በነርሱ ላይም ወደ እስልምና እንዲገቡ ጥሪ እንዲያቀርብላቸው፤ እስልምናን ከተቀበሉት በነርሱ ላይ ያለባቸውን ግዴታ እንዲነግራቸው አዘዙት። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ አላህ የመጣራት ትሩፋቱ አንድ ተጣሪ ለአንድ ሰው መመራት ሰበብ ከሆነ ይህ ለርሱ ዐረቦች ዘንድ ውድ ንብረት የሚባለውን ቀይ ግመል ከሚኖረው ወይም ኑሮት ሰደቃ ከሚሰጠው የበለጠ የተሻለ መሆኑን ለዐሊይ ገለፁለት።

فوائد الحديث

መልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዐሊይን አላህና መልክተኛው እንደሚወዱት እርሱም አላህና መልክተኛውን እንደሚወድ መመስከራቸው የዐሊይን ቢን አቢ ጧሊብ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ ያስረዳናል።

ሶሐቦች ለመልካም ነገር ያላቸውን ጉጉትና እሽቅድድም እንረዳለን።

በውጊያ ወቅትም ቢሆን ስነ-ስርዓት እንደተደነገገና አላስፈላጊ የሆኑ አስደንጋጭ ድምጾችና መራወጥ መተው እንደሚገባ እንረዳለን።

የርሳቸውን ነቢይነትን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሚጠቁሙ ነገሮች መካከል በየሁዶች ላይ ድል እንደሚያደርጉ ተናግረው መከሰቱና በአላህ ፈቃድ በርሳቸው እጅ የዐሊ ቢን አቢጧሊብ አይኖች መፈወሱ ነው።

ከጂሃድ የሚፈለገው ትልቁ አላማ ሰዎች ወደ እስልምና እንዲገቡ ማድረግ ነው።

ዳዕዋ (ጥሪ) ቀስ በቀስ ነው የሚከወነው። ከከሀዲ መጀመሪያ የሚፈለገው ሁለቱን የምስክርነት ቃላቶችን ተናግሮ ወደ እስልምና እንዲገባ ነው። ቀጥሎ ከዚህ በኋላ የእስልምና ግዴታዎችን ይታዘዛል።

ወደ እስልምናና እስልምና ውስጥ ወዳሉ መልካሞች በመጣራት የሚገኘው ትሩፋት ለተጣሪውም ለተጠሪውም ነው። ተጠሪው ቅኑን ጎዳና ያገኛል፤ ተጣሪው ደግሞ ትልቅ ምንዳ ይመነዳል።

التصنيفات

ህክምና፣ መታከምና ሸሪዓዊ ሩቃ, የሶሐቦች (ረዺየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ትሩፋቶች, የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘመቻዎችና ጦርነቶች