إعدادات العرض
የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአቡበከርና ዑመር እንዲህ አሉ: "እነዚህ ሁለቱ ከነቢያትና መልክተኞች ውጪ ከመጀመሪያው…
የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአቡበከርና ዑመር እንዲህ አሉ: "እነዚህ ሁለቱ ከነቢያትና መልክተኞች ውጪ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ካሉ የጀነት ነዋሪ ጎልማሶች አለቆቹ ናቸው።
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአቡበከርና ዑመር እንዲህ አሉ: "እነዚህ ሁለቱ ከነቢያትና መልክተኞች ውጪ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ካሉ የጀነት ነዋሪ ጎልማሶች አለቆቹ ናቸው።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English فارسی Français Русский 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Bahasa Indonesia اردو Hausa Kurdî Português Nederlands Tiếng Việt অসমীয়া ગુજરાતી Kiswahili پښتو සිංහල ไทย Tagalog മലയാളം नेपालीالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አቡበከር አስሲዲቅንና ዑመር አልፋሩቅን (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢያት በኋላ ከሰው ዘር ሁሉ በላጮች እንደሆኑና ከነቢያትና መልክተኞች በኋላም ጀነት ከገቡ ሰዎች በላጮቹ መሆናቸውን ተናገሩ።فوائد الحديث
አቡበከርና ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢያትና መልክተኞች ቀጥለው ከሰው ዘር ሁሉ በላጮቹ ናቸው።
ጀነት ውስጥ ጉልምስና የለም። ይልቁንም ሰዎች ጀነት የሚገቡት የሰላሳ ሶስት አመት ወጣት ሆነው ነው። ከሐዲሡ የተፈለገውም በዱንያ ውስጥ ጎልማሳ ሆነው ከሞቱ ሰዎች አለቃ ናቸው ማለት ነው። ወይም ይህን ሐዲሥ በሚናገሩበት ወቅት በዱንያ ውስጥ ከነበሩበት ጉልምስና አንፃር ነው።