إعدادات العرض
(ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ለሁልሙልኩ ወለሁልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር) የሚለውን ውዳሴ በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ያለ ሰው
(ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ለሁልሙልኩ ወለሁልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር) የሚለውን ውዳሴ በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ያለ ሰው
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "(ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ለሁልሙልኩ ወለሁልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር) የሚለውን ውዳሴ በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ያለ ሰው ለርሱ አስር ባሪያዎችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል፤ መቶ ምንዳም ለርሱ ይጻፍለታል፤ መቶ ኃጢአቶችም ከርሱ ላይ ይሰረዛሉ፤ ቀኑንም እስኪያመሽ ድረስም ለርሱ ከሸይጧን መጠበቂያ ትሆንለታለች፤ እርሱ ከሰራው የበለጠ አብዝቶ የሰራ ሰው ካልሆነ በቀር አንድም ሰው ከርሱ የበለጠም አልሰራም።" ትርጉሙም (ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የሌለውም ነው። ንግስና የርሱ ነው። ምስጋናም ለርሱ ነው። እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው።)
الترجمة
العربية Tiếng Việt Magyar ქართული සිංහල Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Hausa English Português मराठी دری বাংলা ភាសាខ្មែរ Kurdîالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተከታዩን ዚክር ስላለ ሰው እንዲህ ብለው ተናገሩ (ላ ኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ) በተመላኪነቱም፣ በጌትነቱም፣ በስሞቹና በባህሪያቶቹም ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። (ለሁል ሙልኩ) ሁሉም ማስተዳደርና ማስተናበር የርሱ ነው። (ወለሁል ሐምድ) በሚፈጥረውና በሚወስነው ሁሉ ምስጋና የርሱ ነው። (ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር) ያለምንም ከልካይ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው። እርሱ ያልሻውም አይሆንም። በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ደጋግሞ ይህንን ውዳሴ ያለ ሰው ለርሱ አላህ ዘንድ አስር ባሪያዎችን ነፃ ያወጣ ሰው ምንዳ ይፃፍለታል፤ መቶ ምንዳና ጀነት ውስጥ ያለ ደረጃም ይፃፍለታል፤ መቶ ወንጀሎችም ከርሱ ላይ ይሰረዙለታል፤ ፀሐይ በመጥለቋ ምሽቱ እስኪገባ ድረስም ቀኑን ከሸይጧን ማጥመምና ቁጥጥር መከለያ፣ መጠበቂያ፣ መመሸጊያና ጋሻ ትሆንለታለች፤ የትንሳኤ ቀንም እርሱ ከሰራው አብዝቶ ያለ ሰው ካልሆነ በቀር ማንም በላጭ ስራ ይዞ አይመጣም።فوائد الحديث
የተውሒድ ቃል ያላት ደረጃንና የምንዳዋን ትልቅነት እንረዳለን።
የበላይ የሆነው አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ችሮታ ሰፊ መሆኑን እንረዳለን። ይህም ለእያንዳንዱ ሰው ገር የሆነን ዚክር (ውዳሴ) መደንገጉና በዛም ላይ ትልቅን ምንዳ በማስቀመጡ ነው።
ይህንን ዚክር በቀን ውስጥ ከመቶ ጊዜ በላይ ቢል ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰውን መቶ ጊዜ ያለ ሰው የሚያገኘውን ምንዳም ያገኛል በጨመረው ልክም ሌላ ምንዳ ይኖረዋል። ይህም ከተባለው በላይ መጨመሩ ምንም ደረጃ የለውም ወይም ያበላሸዋል ተብሎ መጠኑን መተላለፉ የተከለከለው የቁጥር ገደብ ውስጥ የሚገባ አይደለም።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "የሐዲሡ ጥቅል መልዕክት በግልፅ የሚያስረዳን ይህንን ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰውን ምንዳ በቀን ውስጥ አከታትሎም ይበል ወይም በተለያዩ ስፍራዎች ከፋፍሎም ይበል ወይም የተወሰነውን የቀኑ መጀመሪያ ላይ የተወሰነውን ደግሞ የቀኑ መጨረሻ ላይ ይበል ውዳሴውን መቶ ጊዜ በማለቱ ብቻ ያገኘዋል። ነገር ግን አጠቃላይ ቀኑን ከሸይጧን መጠበቂያ እንዲሆንለት የቀኑ መጀመሪያ ላይ ቢለው በላጭ ነው።"