የሰው ልጅ ሲሞት ከሶስት ስራዎቹ ውጪ ስራዎቹ ከርሱ ይቋረጣሉ። ሰደቀቱል ጃሪያህ (ተሻጋሪ ምፅዋቶቹ) ወይም ጠቃሚ ዕውቀት ያስተላለፈ ወይም ለርሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ያለው…

የሰው ልጅ ሲሞት ከሶስት ስራዎቹ ውጪ ስራዎቹ ከርሱ ይቋረጣሉ። ሰደቀቱል ጃሪያህ (ተሻጋሪ ምፅዋቶቹ) ወይም ጠቃሚ ዕውቀት ያስተላለፈ ወይም ለርሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ያለው ሲቀር ሌሎቹ ስራዎቹ ይቋረጣሉ።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የሰው ልጅ ሲሞት ከሶስት ስራዎቹ ውጪ ስራዎቹ ከርሱ ይቋረጣሉ። ሰደቀቱል ጃሪያህ (ተሻጋሪ ምፅዋቶቹ) ወይም ጠቃሚ ዕውቀት ያስተላለፈ ወይም ለርሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ያለው ሲቀር ሌሎቹ ስራዎቹ ይቋረጣሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሞተ ሰው በመሞቱ ስራው እንደሚቋረጥ፤ ከነዚህ ሶስት ስራዎች ውጪም ከሞተ በኋላ ምንዳ የሚያገኝበት እንደሌለው ተናገሩ። ሶስቱ ስራዎች ግን ሰበባቸው እርሱ ስለሆነ አይቋረጡም። የመጀመሪያው: እንደወቅፍ፣ መስጂድ መገንባት፣ ጉድጓድ መቆፈርና ሌሎች ምንዳቸው የማይቋረጥና የሚዘወትር ምፅዋት ናቸው። ሁለተኛው: ጠቃሚ ዕውቀትን ያስተላለፈ፡ ዕውቀት ሰጢ መጽሐፍትን እንደመፃፍ፣ የሆነን ግለሰብ ማስቀራትና ከሞተ በኋላ ይህ የቀራው ግለሰብ እውቀቱን በማሰራጨት ላይ መሳተፍን የመሰለ ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት ነው። ሶስተኛው: ለወላጆቹ ዱዓ የሚያደርግ አማኝ መልካም ልጅ ነው።

فوائد الحديث

የሰው ልጅ ከሞተ በኋላ የሚደርሰው ምንዳ ተሻጋሪ ምፅዋት፣ በርሱ ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት ያስተላለፈ እና ዱዓ እንደሆነ የእውቀት ባለቤቶች ባጠቃላይ ተስማምተዋል። ልክ እንደዚሁ ሐጅም ከሞተ በኋላ እንደሚደርሰው በሌላ ሐዲሥ መጥቷል።

ሐዲሡ ውስጥ ሶስቱ ብቻ የተጠቀሱት ሶስቱም የመልካም ስራ መሰረቶች ስለሆኑ እና አብዛኛው ጊዜ ባለፀጋዎቹ ከነርሱ ህልፈት በኋላ ይቀራሉ ብለው የሚያስቧቸው እነዚህን ስለሆነ ነው።

ማንኛውም ሰዎች በርሱ የሚጠቀሙበት እውቀት ምንዳ ይገኝበታል። ነገር ግን ዋናውና ቁንጮው ሸሪዓዊ እውቀትና የሸሪዓን እውቀት ለመረዳት የሚያግዙ እውቀቶች ናቸው።

እውቀት ከሶስቱም እጅግ ጠቃሚው ነው። ምክንያቱም በእውቀት የሚማረው ሰው ይጠቀምበታል፤ በእውቀት ሸሪዓን መጠበቅ ይገኝበታል፤ በእውቀት ፍጡራን ባጠቃላይ ይጠቀማሉ። እውቀት አዳራሽና አጠቃላይ ነው። በህይወት እያለህ ያሉትም ይሁኑ ከሞትክ በኋላ ያሉትም ትተህ ያለፍከው እውቀትህን ይቀስማሉ።

መልካም ልጆችን በማነፅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። በመጪው አለም ወላጆቻቸውን የሚጠቅሙት እነርሱ ናቸውና። ከመልካም ልጆች ጥቅም መካከል ለወላጆቻቸው የሚያደርጉት ዱዓ አንዱ ነው።

ወላጆች ከሞቱ በኋላ ለነርሱ በጎ በመስራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህ እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ ልጅም ጭምር የሚጠቀምበት በጎ ስራ ነው።

ከልጅ ውጪ ቢሆን ራሱ ለሞተ ሰው ዱዓ ማድረግ ሟችን ይጠቅማል። ነገር ግን ተለይቶ ልጅ የተጠቀሰው አብዛኛው ጊዜ እስኪሞት ድረስ ሳያቋርጥ ለአንድ ሰው ዱዓ ሊያደርግ የሚችለው ልጅ ስለሆነ ነው።

التصنيفات

ወቅፍ, የዱዓእ ትሩፋቶች, Doing Good Deeds on behalf of the Deceased and Gifting them the Reward, Merit and Significance of Knowledge