إعدادات العرض
1- የወርቅና የብር ባለቤት ሆኖ ሐቃቸውን የማይወጣ ሰው የትንሳኤ ቀን ለርሱ የእሳት ዝርግ ተዘርግቶለት በርሷ በጀሃነም እሳት ውስጥ ሳይቃጠል የሚቀር የለም። ጎኑም፣ ግንባሩና ጀርባውም የሚተኮስ መሆኑ አይቀርም።
2- የሰው ልጅ ሲሞት ከሶስት ስራዎቹ ውጪ ስራዎቹ ከርሱ ይቋረጣሉ። ሰደቀቱል ጃሪያህ (ተሻጋሪ ምፅዋቶቹ) ወይም ጠቃሚ ዕውቀት ያስተላለፈ ወይም ለርሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ያለው ሲቀር ሌሎቹ ስራዎቹ ይቋረጣሉ።