የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሰዕድ እናት ሞተች ማንኛው ምፅዋት ነው በላጩ? እርሳቸውም "ውሃ" አሉ። እርሱም ጉድጓድ ቆፈረና "ይህቺ ለሰዕድ እናት ነው።" አለ።

የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሰዕድ እናት ሞተች ማንኛው ምፅዋት ነው በላጩ? እርሳቸውም "ውሃ" አሉ። እርሱም ጉድጓድ ቆፈረና "ይህቺ ለሰዕድ እናት ነው።" አለ።

ከሰዕድ ቢን ዑባዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሰዕድ እናት ሞተች ማንኛው ምፅዋት ነው በላጩ? እርሳቸውም "ውሃ" አሉ። እርሱም ጉድጓድ ቆፈረና "ይህቺ ለሰዕድ እናት ነው።" አለ።»

الشرح

የሰዕድ ቢን ዑባዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እናት ሞተች። ለናቱ ሊመፀውት የሚችለው በላጩ የምፅዋት አይነት የትኛው እንደሆነም ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠየቃቸው። እርሳቸውም በላጩ ምፅዋት ውሃ እንደሆነ ነገሩት። እርሱም ጉድጓድ ቆፈረና ለእናቱ ምፅዋት አደረጋት።

فوائد الحديث

ውሃ በላጩ የምፅዋት አይነት መሆኑ መገለፁን እንረዳለን።

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሰዕድ ውሃ እንዲመፀውት መጠቆማቸው ጥቅሙ ዲናዊንም ዱንያዊንም አላማ ስለሚያጠቃልል፤ ሀሩሩ የሚበረታ በመሆኑ፤ ከፍተኛ ፍላጎት እያለ የውሃ እጥረት በመኖሩ ነው።

ይህ ሐዲሥ የሶደቃ ምንዳ ወደ ወላጆች እንደሚደርስ ይጠቁማል።

ሰዕድ ቢን ዑባዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ለወላጁ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና በጎ ማድረጉን እንረዳለን።

التصنيفات

ወቅፍ, የፈቃደኝነት ምፅዋት (ሶደቃ)