إعدادات العرض
አዋቂ (ዐሊም) አላህን አብዝቶ ከሚገዛ ባሪያ (ከዐቢድ) ጋር ያለው ልዩነት እኔ ከናንተ መካከል ከዝቅተኛው ሰው ጋር እንዳለኝ ልዩነት ነው።
አዋቂ (ዐሊም) አላህን አብዝቶ ከሚገዛ ባሪያ (ከዐቢድ) ጋር ያለው ልዩነት እኔ ከናንተ መካከል ከዝቅተኛው ሰው ጋር እንዳለኝ ልዩነት ነው።
አቡ ኡማመተል ባሂሊይ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና - እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: «ለአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለሁለት ሰዎች ተነገራቸው። አንደኛው አላህን አብዝቶ የሚገዛ ሲሆን ሌላኛው ዓሊም (አዋቂ) ነው። የአላህ መልክተኛም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "አዋቂ (ዐሊም) አላህን አብዝቶ ከሚገዛ ባሪያ (ከዐቢድ) ጋር ያለው ልዩነት እኔ ከናንተ መካከል ከዝቅተኛው ሰው ጋር እንዳለኝ ልዩነት ነው።" ቀጥለው የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ "አላህ፣ መልአክቶቹና፣ ጓድጓዷ ውስጥ ያለች ጉንዳን፣ ዓሳ እንኳን ሳትቀር የሰማያትና የምድር ነዋሪዎች መልካም በሚያስተምሩ ላይ ሶላት ያወርዳሉ።"»
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული සිංහල Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Hausa Português मराठी دری বাংলা ភាសាខ្មែរالشرح
የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ሁለት ሰዎች ተወሱ። አንዱ ዓቢድ (አላህን አብዝቶ የሚገዛ) ሲሆን ሌላኛው ዐሊም (አዋቂ) ነው። ማንኛቸው ይበልጣል ተብለው ተጠየቁ። ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፡ "የሸሪዓን እውቀቶች አውቆ በእውቀቱ ከመስራት አልፎ የሚያስተምር ሰው ማወቅ ያለበትን ግዴታዎች አውቆ ራሱን ለአምልኮ ብቻ ነፃ ካደረገ ሰው ጋር ያለው ልዩነት ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሶሓቦች ሁሉ ዝቅተኛ ከሆነው ጋር እንዳላቸው ልዩነትና ደረጃ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የዚህን ምክንያት እንዲህ በማለት ገለፁ። አላህ ሱብሓነሁ፣ የዐርሽ ተሸካሚ የሆኑ መልአክቶቹ፣ የተቀሩትም ሰማይ ውስጥ የሚኖሩ መልአክቶች፣ በምድር የሚኖሩ ሰዉም ጂንም አጠቃላይ እንስሶችም፣ ጉንዳን እንኳን ከምድር በታች ባለው ቤቷ ሳይቀር፣ አሳና የባህር እንስሶችም ሳይቀሩ የየብሱም ይሁን የባህሩ እንስሶች ባጠቃላይ እነዚህ ሁሉ መዳኛቸውና መድህናቸው የሆነውን መልካም ነገርና ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ለሚያስተምር ሰው ዱዓ ያደርጋሉ።فوائد الحديث
ወደ አላህ ዳዕዋ ከማድረጊያ መንገዶች መካከል ማነሳሳትና ምሳሌዎችን ማድረግ አንዱ ነው።
እውቀትን የተማሩና ባወቁት በመስራትና ወዳወቁት በመጣራት ላይ የእውቀትን ሐቅ የተወጡ ዑለማዎችን ደረጃና ልቅና እንረዳለን።
ዑለማዎችንና እውቀት ፈላጊዎችን በማክበርና ለነርሱ ዱዓ በማድረግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ሰዎችን መልካም ነገር በማስተማር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህም የደስታቸውና የመዳናቸው ምክንያት ነውና።
التصنيفات
የእውቀት ትሩፋት