إعدادات العرض
አላህ በርሱ የላከኝ ቅናቻና እውቀት ምሳሌው መሬት ላይ እንደወረደ ብዙ ዝናብ ምሳሌ ነው።
አላህ በርሱ የላከኝ ቅናቻና እውቀት ምሳሌው መሬት ላይ እንደወረደ ብዙ ዝናብ ምሳሌ ነው።
ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "አላህ በርሱ የላከኝ ቅናቻና እውቀት ምሳሌው መሬት ላይ እንደወረደ ብዙ ዝናብ ምሳሌ ነው። ዝናቡ ካገኘው መሬት መካከል ውሃውን የመጠጠች፣ በዛውም ደረቅ ሳርና በርካታ እርጥብ ሳሮችን ያበቀለች ለምለም መሬት አለች፤ የዘነበውን ውሃ የምታቁርና አላህ በርሷ ሰዎችን የሚጠቅምበት ከርሷም የሚጠጡባት፣ ከብቶቻቸውንና ዘራቸውንም የሚያጠጡበት ደረቅ መሬትም አለች፤ ይህቺ ዝናብ ሌላም የመሬትን ክፍል አግኝታለች። ይህም የመሬት ክፍል ወይ ውሃን አያቁር ወይ ሳር አያበቅል የሆነ ለጥ ያለ ደረቅ መሬት ነው። ይህም ምሳሌ አላህ እኔን የላከበት የሆነውን የአላህን ሃይማኖት ተገንዝቦ አላህ በዲኑ ተጠቃሚ ያደረገው፤ ተምሮም ያስተማረ ሰው ምሳሌ እና ለዚህ አላህ እኔን የላከበት ለሆነው ሃይማኖት ራሱንም ቀና ያላደረገ የአላህንም ቅን መመርያ ያልተቀበለ ሰው ምሳሌ ነው።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላማ ላይ የሚያደርስ የሆነውን እርሳቸው ይዘውት በመጡት መንገድና መመሪያ እንዲሁም ሸሪዓዊ እውቀት የሚጠቀምን ሰው ሁኔታው አስገርሟቸው ብዙ ዝናብ በሚዘንብበት ምድር ምሳሌ አደረጉት። ይህ የምድር ክፍልም ሶስት ክፍሎች አሉት። የመጀመሪያውም: የዝናብን ውሃ የምትቀበልና ደረቁንም ይሁን እርጥቡን ቡቃያ የምታበቅል ሰዎችም በርሷ የሚጠቀሙባት ምርጥና ለምለም መሬት ናት። ሁለተኛዋም: መሬቷ አዝርዕት ባታበቅልም ቢያንስ ውሃን የምታቁር ናት። ይህቺም መሬት ሰዎች እንዲጠቀሙባት ውሃን ትይዛለች። ሰዎችም ይጠጡባታል፣ እንስሶቻቸውንና አዝርዕታቸውንም ያጠጡባታል። ሶስተኛው: ቀጥ ያለች እና ለስላሳ መሬት ናት። ውሃንም አትይዝም። አዝርዕትንም አታበቅልም። ይህቺም መሬት ለራሷም በዚህ ውሃ አልተጠቀመች፤ ሰዎችም በርሷ አልተጠቀሙም። ልክ እንደዚሁ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የተላኩበትን እውቀትና መመሪያ የሚሰሙ ሰዎች ሶስት ክፍሎች አላቸው። የመጀመሪያው: የአላህን ሃይማኖት ያወቀና የተገነዘበ፣ በእውቀቱ የሚሰራና ሌላውንም የሚያስተምር ነው። ይህም ልክ እንደምርጥ መሬት ምሳሌ ነው። ለራሷም ዝናቡን ጠጥታ ተጠቅማለች። ቡቃያን አብቅላም ሌላውን ጠቅማለች። ሁለተኛው: እውቀትን ሸምድዷል ነገር ግን ከሚያውቀው እውቀት ግንዛቤና አስተምህሮቶችን ማውጣጣት አይችልም። እውቀትን ሰብስቧል። በዘመኑ የሚያስፈልግን እውቀትን አጠቃሎ አውቋል። ነገር ግን እውቀቱ ፍሬያማ አይደለም ወይም ሰብስቦ የሸመደደውን አልተረዳውም። እርሱ ለሌሎች መሳሪያ ነው የሆነው። የዚህም ምሳሌ ውሃ የሚጠራቀምበትና ሰዎችም በውሃው እንደሚጠቀሙበት መሬት ምሳሌ ነው። ሶስተኛው: እውቀትን እየሰማ የማይሸመድድ፣ በርሱም የማይተገብርና ለሌላውም የማያስተላልፍ ሰው ነው። የዚህም ሰው ምሳሌ ቡቃያም የማያበቅል፣ ውሃንም የማያቁርና የማይቀበል ወይም ሌላው እንዳይጠቀመው ውሃውን የሚያበላሽ የሆነ እንደለስላሳ መሬት ምሳሌ ነው።فوائد الحديث
እውቀትን የመፈለግና የማስተማር ደረጃው መገለፁንና እውቀትን ከመፈለግና ከማስተማር መዞር ዛቻ የመጣበት መሆኑን እንረዳለን።
ሃሳቡን ሰዎች ሀሳቡን እንዲረዱት ምሳሌን መስጠት እንደሚገባ እንረዳለን።
ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: "ዝናብ የሞተን አገር ህያው እንደሚያደርገው ሁሉ ልክ እንደዚሁ የዲን እውቀቶች የሞተን ቀልብ ህያው ያደርጋሉ። ሐዲሡ በመቀጠል የዲን እውቀትን የሚያዳምጡ ሰዎችን ዝናብ በሚዘንብባቸው በተለያዩ የመሬት ክፍሎች መሰላቸው።"
ሰዎች ሸሪዓዊ እውቀትን በመውሰድ ረገድ የተለያዩ ደረጃዎች አላቸው።
التصنيفات
የእውቀት ትሩፋት