'እስክታምኑ ድረስ ጀነት አትገቡም። እስክትዋደዱ ድረስም አታምኑም። የፈፀማችሁት ጊዜ የምትዋደዱበትን አንዳች ነገር ልጠቁማችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አሰራጩ።'

'እስክታምኑ ድረስ ጀነት አትገቡም። እስክትዋደዱ ድረስም አታምኑም። የፈፀማችሁት ጊዜ የምትዋደዱበትን አንዳች ነገር ልጠቁማችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አሰራጩ።'

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'እስክታምኑ ድረስ ጀነት አትገቡም። እስክትዋደዱ ድረስም አታምኑም። የፈፀማችሁት ጊዜ የምትዋደዱበትን አንዳች ነገር ልጠቁማችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አሰራጩ።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአማኞች በስተቀር ማንም ጀነት እንደማይገባ፤ ከፊሉ ከፊሉን እስኪወድ ድረስም ኢማን እንደማይሞላና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሁኔታም እነደማይስተካከል ገለፁ። ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሱ አማካኝነት ውዴታ የሚዳረስበትን በላጭ ነገር ጠቆሙ። እርሱም: በሙስሊሞች መካከል አላህ ለባሮቹ ሰላምታ መለዋወጫ ያደረገውን ሰላምታን ማሰራጨት ነው።

فوائد الحديث

በእምነት ካልሆነ በቀር ጀነት መግባት እንደሌለ እንረዳለን።

የትኛውም ሙስሊም ለነፍሱ የሚወደውን ለወንድሙ መውደዱ ከኢማን መሟላት መገለጫዎች መካከል አንዱ ነው።

ለሙስሊሞች ሰላምታን ማብዛትና መለዋወጥ በሰዎች መካከል ውዴታንና ደህንነትን ስለሚያሰራጭ ይወደዳል።

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "በመካከላችሁ" ስላሉ "አሰላሙ ዓለይኩም" ከሙስሊም ጋር ካልሆነ በቀር አይባልም።

ሰላምታን መለዋወጥ መቆራረጥን፣ መኮራርፍንና መጣላትን ያስወግዳል።

በሙስሊሞች መካከል የመዋደድን አንገብጋቢነት እንረዳለን። እርሱም ኢማንን ከሚሞሉ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።

በሌላ ሐዲሥ የተሟላው የሰላምታ ይዘት "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ" እንደሆነ መጥቷል። "አስሰላሙ ዐለይኩም" የሚለውም በቂ ነው።

التصنيفات

የአካል ተግባራት ትሩፋቶች, የአካል ተግባራት ትሩፋቶች