إعدادات العرض
ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።
ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።
ከዐብደላህ ቢን ቡስር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው «አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የእስልምና ድንጋጌዎች በርግጥም በኔ ላይ በዙብኝ። አጥብቄ የምይዘውን አንዳች ነገር ይንገሩኝ።" እርሳቸውም እንዲህ አሉ: "ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Nederlands অসমীয়া Tiếng Việt Kiswahili ગુજરાતી پښتو Oromoo ไทย Română മലയാളം Malagasy नेपाली Deutschالشرح
አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከደካማነቱ አንፃር ግዴታ ያልሆኑ አምልኮዎች እስኪያቅቱት ድረስ መብዛታቸው እንደተሰማው ስሞታ አቀረበ። ቀጥሎም ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ብዙ ምንዳ የሚያመጣለት የሆነን አጥብቆ የሚይዘውን ቀላል ስራ እንዲጠቁሙት ጠየቀ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሁሉም ሁኔታና ወቅት ምላሱ በ"ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ በ"ተሕሚድ" (አልሐምዱሊላህ)፣ ምህረት በመጠየቅ (አስተጝፊሩሏህ)፣ ዱዓ በማድረግና በመሳሰሉት አላህን በማውሳት ዘውትሮ ምላሱን ማንቀሳቀስና ማርጠብ እንዳለበት ጠቆሙት።فوائد الحديث
አላህን በማውሳት ላይ መዘውተር ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
ከአላህ ችሮታ መካከል ትልቁ የምንዳን ምክንያት ማቅለሉ ተጠቃሽ ነው።
ባሮች በበጎና መልካም እጣ ፈንታቸው እንደሚበላለጡ እንረዳለን።
እንደ "ሱብሐነላህ"፣ "አልሐምዱሊላህ"፣ "ላኢላሃ ኢለላህ"፣ "አላሁ አክበር"ና ከዚህም ውጪ ያሉ አዝካሮችን ከቀልብ ጋር በማስተሳሰር በምላስ አላህን አብዝቶ ማውሳት የብዙ ግዴታ ያልሆኑ (ሱና) አምልኮዎችን ደረጃ ይይዛል።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሁሉም ጠያቂዎች የሚስማማቸውን መልስ እየጠበቁ መመለሳቸውን እንረዳለን።
التصنيفات
የዚክር ትሩፋቶች