إعدادات العرض
አላህ ለርሱ ፊት ብቻ ተብሎና ጥርት ተደርጎ የተሰራ ስራን ካልሆነ በቀር አይቀበልም።" አሉ።
አላህ ለርሱ ፊት ብቻ ተብሎና ጥርት ተደርጎ የተሰራ ስራን ካልሆነ በቀር አይቀበልም።" አሉ።
ከአቡ ኡማማ አልባሂሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመምጣት እንዲህ አለ: "ምንዳንም መወደስንም ፈልጎ የዘመተ ሰው ለርሱ አላህ ዘንድ ምን እንዳለው ንገሩኝ?" የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመልሱ "ምንም የለውም!" አሉ። ሶስት ጊዜ ደጋግሞ ጠየቃቸው የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመልሱ "ለርሱ ምንም የለውም!" ይሉ ነበር። ቀጥለውም "አላህ ለርሱ ፊት ብቻ ተብሎና ጥርት ተደርጎ የተሰራ ስራን ካልሆነ በቀር አይቀበልም።" አሉ።»
الترجمة
العربية অসমীয়া Bahasa Indonesia Kiswahili Tagalog Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands සිංහල Hausa پښتو ไทย नेपाली اردو Кыргызча മലയാളം Englishالشرح
አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለጂሀድና ለጦርነት ከአላህም ምንዳን ፈልጎ ሰዎች ዘንድም መሞገስና መወደስን ከጅሎ ስለሚወጣ ሰው ብይን ሊጠይቅ ፈታዋ ፈልጎ መጣ። ምንዳ ያገኛልን? ሲልም ጠየቃቸው። የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኒያው ከአላህ ውጪ ስላጋራ ለርሱ አንዳችም ምንዳ እንደሌለው መለሱለት። ሰውዬውም ሶስት ጊዜ ጥያቄውን ደገመላቸው። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለርሱ ምንም ምንዳ እንደሌለው አፅንዖት በመስጠት ተመሳሳይ መልስ መለሱለት። ቀጥለውም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የትኛውም ስራ አላህ ዘንድ ምንዳና ተቀባይነት የሚያገኝበትን መርህ ነገሩት። የትኛውም ስራ በአላህ ላይ አንድም ሳይጋራበት ሙሉ በሙሉ ለአላህ የሆነና ለርሱ ፊት ብቻ ተብሎ የተሰራ እስካልሆነ ድረስ አላህ ስራውን እንደማይቀበለው ነገሩት።فوائد الحديث
አላህ ለርሱ ጥርት ተደርጎና በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ መሰረት የተሰራ ስራ እስካልሆነ ድረስ ስራዎችን አይቀበልም።
የአንድ ፈትዋ ሰጪ ዓሊም መልስ የተሻለ የሚሆነው ፈትዋው የጠያቂውን አላማ ከማሟላት አልፎ ጭማሪ ነጥቦችን ሲያካትት ነው።
ትልቅ ጉዳይን ስለርሱ ደጋግሞ በመጠየቅ አፅንዖት መስጠት እንደሚገባ እንረዳለን።
ትክክለኛ ታጋይ የሚባለው የአላህ ንግግር የበላይ እንዲሆን፣ ኒያን ከማጥራት ጋር የመጪውን አለም ምንዳና አጅርን በመፈለግ የተዋጋ ነው እንጂ ለዱንያ አላማ ብሎ የተዋጋ ሰው አይደለም።
التصنيفات
የቀልብ ተግባራት ትሩፋቶች