በድርና ሑደይቢያ ላይ የተሳተፈ ሰው እሳት አይገባም።

በድርና ሑደይቢያ ላይ የተሳተፈ ሰው እሳት አይገባም።

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "በድርና ሑደይቢያ ላይ የተሳተፈ ሰው እሳት አይገባም።"»

[ሶሒሕ ነው።] [አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሂጅራ በሁለተኛው ዓመት የተካሄደችውን የበድር ዘመቻ ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጋር ሆኖ ለመዋጋት የተሳተፈና በስድስተኛው አመተ ሂጅራ የተከሰተችውን የውዴታው ቃልኪዳን የነበረበትን የሑደይቢያን ስምምነት የተሳተፈ ሰው እሳት እንደማይገባ ተናገሩ።

فوائد الحديث

ይህ ሐዲሥ የበድርና የሑደይቢያ ተሳታፊዎችን ደረጃ ያስረዳናል። እነርሱም እሳት አይገቡም።

አላህ እነርሱን ከበዳይነት (ሊጠብቃቸው) ኃላፊነት እንደወሰደላቸው፤ በኢማን ላይ መሞትን እንደሚገጥማቸው፤ የእሳት ቅጣት ሳይነካቸውም ጀነት እንደሚያስገባቸው መገለፁን እንረዳለን። ይህም አላህ ለሻው የሚሰጠው የአላህ ችሮታ ነው። አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው።

التصنيفات

የሶሐቦች (ረዺየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ, የሶሐቦች (ረዺየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃዎች, የሶሐቦች (ረዺየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ትሩፋቶች