إعدادات العرض
ሙፈሪዶች ቀደሙ!
ሙፈሪዶች ቀደሙ!
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመካ መንገድ ላይ እየተጓዙ ሳለ ጁምዳን በሚባል ተራራ ላይ ሲያልፉ እንዲህ አሉ: "ይህ ጁምዳን ነው ተጓዙ! ሙፈሪዶች ቀደሙ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሙፈሪዶች እነማን ናቸው?" አሉ። እርሳቸውም "አላህን በብዛት የሚያወሱ ወንዶችና ሴቶች ናቸው።" አሉ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी සිංහල ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Kiswahili Português دری অসমীয়া Tiếng Việt Svenska ไทย Yorùbá Кыргызча ગુજરાતી नेपाली Română മലയാളം Nederlands Oromoo తెలుగు پښتو Soomaali Kinyarwanda Malagasy ಕನ್ನಡالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህን በብዛት የሚያወሱ ሰዎች እነርሱ የተነጠሉና በዘውታሪዋ ጀነት ውስጥ ከፍተኛን ደረጃ በማግኘት ሌሎችን የቀደሙ መሆናቸውን በመጥቀስ ደረጃቸውን ገለፁ። ከሌሎች ተራራ ተነጥሎ በሚገኘው የጁምዳን ተራራም መሰሏቸው።فوائد الحديث
ዚክር ማብዛትና በርሱ መጠመድ ተወዳጅ እንደሆነ እንረዳለን። በአኺራ መቅደም የሚገኘውም ታዛዥነትን በማብዛትና አምልኮን በማጥራት ነው።
አላህን ማውሳት በምላስ ብቻ ይተገበራል ወይም በልብ ብቻም ይተገበራል ወይም በምላስና በልብ በጋራ ይተገበራል። ይህም ከፍተኛው ደረጃ ነው።
ከዚክር መካከል በሸሪዓ በጊዜ ተገድበው የመጡ የንጋትና የምሽት አዝካሮች፣ ከግዴታ ሶላቶች በኋላና በሌሎችም ወቅቶች የሚባሉ የለት ተዕለት አዝካሮች ይጠቀሳሉ።
ነወዊ እንዲህ ብለዋል: የዚክር ደረጃ በተስቢሕ፣ በተህሊል፣ በተሕሚድ፣ በተክቢርና በመሳሰሉት ላይ ብቻ የተገደበ እንዳልሆነ እወቅ! እንደውም ሁሉም ለአላህ ብለው የሆነ አምልኮ የሚሰሩ ባጠቃላይ አላህን አወሱ ይባላሉ።
አላህን ማውሳት ከፅናት ምክንያቶች መካከል ትልቁ ነው። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ እንዲህ ብሏል {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሰራዊትን በገጠማችሁ ጊዜ ፅኑ፤ (መክቱ)። አላህንም በብዙ አውሱ፤ በእርግጥ ትድናላችሁና።} [አልአንፋል:45]
አላህን በሚያወሱና በጁምዳን ተራራ መካከል የሚያመሳስላቸው መነጠልና ገለል ማለታቸው ነው። የጁምዳን ተራራ ከተራሮች ነጠል ያለ እንደሆነው ሁሉ አላህን የሚያወሱም የተነጠሉ ናቸው። የተነጠለ ሲባል በሰዎች መካከል ቢሆን እንኳ ልቡና ምላሱ ጌታውን በማውሳት የተነጠለ፣ ከሰዎች በተገለለ ጊዜም በዚክር የተደሰተ፣ ከሰዎች ጋር አብዝቶ ሲቀላቀልም (አላህን ከማውሳት በመራቁ) ብቸኝነት የተሰማው ማለት ነው። የተመሳሰሉት ተራራ ለመሬት መርጋት ሰበብ እንደሆነው ዚክር በሃይማኖት ላይ ለመፅናት ምክንያት ስለሆነም ይሆናል። ወይም በዱንያና በአኺራ ወደ መልካም በመቅደሙም ይሆናል። ይህም ከመዲና ወደ መካ የሚጓዝ ሰው ጁምዳን ጋር የደረሰ ጊዜ ወደ መካ መድረሱ ምልክት እንደሆነና ጁምዳን ጋር የደረሰ ሰው ቀዳሚ እንደሚሆነው ልክ እንደዚሁ አላህን የሚያወሳ ሰውም አብዝቶ አላህን በማውሳቱ ሌላውን ቀዳሚ ስለሆነ ነው። አላህ የበለጠ ዓዋቂ ነው።
التصنيفات
የዚክር ትሩፋቶች