ቁርኣንን ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነብ ምፅዋትን በይፋ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው፤ ቁርኣንን በዝግታ የሚያነብ ምፅዋትን በድብቅ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው።

ቁርኣንን ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነብ ምፅዋትን በይፋ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው፤ ቁርኣንን በዝግታ የሚያነብ ምፅዋትን በድብቅ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው።

ዑቅባ ቢን ዓሚር አልጁሀኒይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "ቁርኣንን ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያነብ ምፅዋትን በይፋ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው፤ ቁርኣንን በዝግታ የሚያነብ ምፅዋትን በድብቅ እንደሚመፀውት አምሳያ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ ዘግበውታል።]

الشرح

ቁርኣንን በይፋ የሚያነብ ምፅዋት በይፋ እንደሚሰጥ አምሳያ መሆኑን፤ ቁርኣንን በድብቅ የሚያነብ ምፅዋት በድብቅ እንደሚሰጥ አምሳያ መሆኑን ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ገለፁ።

فوائد الحديث

ድምፅን ከፍ አድርጎ ወደ ማንበብ ያነሳሳን ጥቅምና ጉዳይ ከሌለ ለምሳሌ ቁርኣንን ማስተማር ይመስል፤ ምፅዋትን መደበቅ በላጭ እንደሆነው ሁሉ ቁርኣንንም በዝግታ ማንበብ በላጭ ነው። ይህም ኢኽላስና ከይዩልኝና በራስ ከመደነቅ መራቅ ስለሚገኝበት ነው።

التصنيفات

የተከበረው ቁርአን ትሩፋቶች, የተከበረው ቁርአን ትሩፋቶች, የቀልብ ተግባራት ትሩፋቶች, የቀልብ ተግባራት ትሩፋቶች, የተከበረው ቁርአንን የማንበብ ስነ-ስርዓት, የተከበረው ቁርአንን የማንበብ ስነ-ስርዓት