እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ ተመለሱ (ተውበት አድርጉ)፤ እኔ በቀን መቶ ጊዜ ወደርሱ እመለሳለሁ (ተውበት አደርጋለሁ።)

እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ ተመለሱ (ተውበት አድርጉ)፤ እኔ በቀን መቶ ጊዜ ወደርሱ እመለሳለሁ (ተውበት አደርጋለሁ።)

ከአልአገርሪ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦች መካከል አንዱ ነበር። እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ ተመለሱ (ተውበት አድርጉ)፤ እኔ በቀን መቶ ጊዜ ወደርሱ እመለሳለሁ (ተውበት አደርጋለሁ።)"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰዎች ተውበትና ምህረት መጠየቅን እንዲያበዙ አዘዙ። እርሳቸው የቀደመውም ሆነ የወደፊት ወንጀላቸው የተማረ ከመሆኑም ጋር እሳቸውም በቀን ከመቶ ጊዜ በላይ ወደ አላህ ተውበት እንደሚያደርጉና ምህረት እንደሚጠይቁ ተናገሩ። ይህም ለአላህ ያላቸውን የተሟላ መዋደቅና የተሟላ ባርነትን የሚያሳይ ነው።

فوائد الحديث

እያንዳንዱ የኢማን ደረጃው ከፍ ያለ ቢሆን እራሱ ወደ አላህ መመለስ ይገባዋል። ሁሉም ሰው የአላህን ሐቅ ከመወጣት በኩል ያጎደለው ነገርም ሳይኖር አይቆርምና ነፍሱን በተውበት ማሟላት ይገባዋል። {ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ።}

ክልክሎችንና ወንጀሎችን ለፈፀመም ይሁን ግዴታዎችን ከመፈፀም ያጓደለም ባጠቃላይ ተውበት ማድረግ ይገባዋል።

ተውበት ሲያደርጉ ለአላህ አጥርቶ ማድረግ ተውበቷ ተቀባይነት እንድታገኝ መስፈርቷ ነው። ከአላህ ውጪ ለሆነ አካል ወንጀልን የተወ ሰው ተውበት አደረገ አይባልም።

ነወዊይ እንዲህ አሉ: "ተውበት ሶስት መስፈርቶች አሉት። ከወንጀሉ መውጣት፣ ወንጀሉን በመፈፀሙ መፀፀት፣ ወደመሰል ወንጀሎች ላይመለስ ቁርጠኛ የሆነ ውሳኔ መወሰን ናቸው። ወንጀሏ ከሰው ልጅ ጋር ተያያዥነት ካላት አራተኛ መስፈርት አላት። እርሱም: የሰራውን በደል ወደ ባለቤቱ መመለስ ወይም ከርሱ መጥራትን ማስገኘት ነው።

የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ምህረት መጠየቅ ለሰሩት ወንጀል መሆን እንደማይጠበቅበት መገንዘብ ያስፈልጋል። ይልቁንም ይህ ባርነታቸው የተሟላ ስለሆነ፤ አላህን በማውሳት ልባቸው የተንጠለጠለች ስለሆነ፤ የአላህ ሐቅ ትልቅ እንደሆነ ለማሳወቅ፤ ባሪያው ምንም ያህል ቢሰራ የአላህን ፀጋ ማጓደሉ እንደማይቀር ለመግለፅ፤ ከርሳቸው በኋላ ለኡመታቸው ከመደንገግ አኳያና ከዚህም ውጪ በርካታ ጥበቦችን ይዟል።

التصنيفات

የዚክር ትሩፋቶች, ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዚክር ዙሪያ ያላቸው መመሪያ