ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አስር የቁርኣን አንቀፆችን ተምረው በተማሩት አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀትና ተግባር ሳይረዱ ሌላ ተጨማሪ…

ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አስር የቁርኣን አንቀፆችን ተምረው በተማሩት አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀትና ተግባር ሳይረዱ ሌላ ተጨማሪ አስር አንቀፆችን አይማሩም ነበር

አቢ ዐብዲረሕማን አስሱለሚይ አላህ ይዘንላቸው እንዲህ አሉ፦ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰሐቦች መካከል ቁርኣን ያስተምረን የነበረ አንድ ሰሐባ "ሶሀቦች ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አስር የቁርኣን አንቀፆችን ተምረው በተማሩት አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀትና ተግባር ሳይረዱ ሌላ ተጨማሪ አስር አንቀፆችን አይማሩም ነበር። በዚህም "ዕውቀትንም ተግባርንም ተማርን" አሉ።" ብሎ ነገረን።

[ሐሰን ነው።] [አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ሰሐቦች -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አስር የቁርኣን አንቀፆችን ይቀስሙ ነበር። በቀሰሙት አስር አንቀፆች ውስጥ ያለውን ዕውቀት እስኪረዱና እሱን ሳይተገብሩ ወደ ሌላ እውቀት አይሸጋገሩም ነበር።

فوائد الحديث

የሰሐቦች -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- ደረጃና ቁርኣንን የመማር ጉጉታቸውን፤

ቁርኣንን መማር የሚባለው በመረዳትና ውስጡ ባለው በመተግበር ነው እንጂ በማንበቡና በመሸምደዱ ብቻ አይደለም።

ዕውቀት ከንግግርና ከተግባር በፊት እንደሆነ ተረድተናል።

التصنيفات

የተጅዊድ እውቀት, የቁርአን አቀራርና የመሸምደዱ ስነ-ስርዓቶች, የእውቀት ትሩፋት