إعدادات العرض
አላህ ለናንተ የምትመፀውቱበትን ነገር አላደረገላችሁምን? ሁሉም ተስቢሕ (ሱብሓነሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተክቢር (አላሁ አክበር) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ)…
አላህ ለናንተ የምትመፀውቱበትን ነገር አላደረገላችሁምን? ሁሉም ተስቢሕ (ሱብሓነሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተክቢር (አላሁ አክበር) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተህሊል (ላኢላሃ ኢለሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከባሌቤታችሁ ጋር ግንኙነት በመፈፀማችሁ ሶደቃ ይገኛል።" አሉ።
ከአቡ ዘር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረቦች መካከል የተወሰኑት ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሀብት ባለቤቶች በምንዳ ጥለውን ሄዱ። እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ፤ እንደምንጾመው ይጾማሉ፤ በትርፍ ገንዘቦቻቸው ይመፀውታሉ።" እርሳቸውም "አላህ ለናንተ የምትመፀውቱበትን ነገር አላደረገላችሁምን? ሁሉም ተስቢሕ (ሱብሓነሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተክቢር (አላሁ አክበር) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተህሊል (ላኢላሃ ኢለሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከባሌቤታችሁ ጋር ግንኙነት በመፈፀማችሁ ሶደቃ ይገኛል።" አሉ። ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን ስሜቱን ስላበረደ በርሷ ምንዳ ይኖረዋልን?" አሉ። እርሳቸውም "እስኪ ንገሩኝ ብልቱን ሐራም ላይ ቢያኖራት ኖሮ ወንጀል አይኖርበትም ነበርን? ልክ እንደዚሁ የተፈቀደችለት ባለቤቱ ላይ ያኖራት ጊዜም ለርሱ ምንዳ ይኖረዋል።" አሉ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Kiswahili Tiếng Việt অসমীয়া ગુજરાતી Nederlandsالشرح
አንዳንድ ድሃ ሶሐቦች ያሉበትን ሁኔታና ድህነታቸውን፣ ብዙ ገንዘብ ያላቸው ወንድሞቻቸው ሶደቃ በመስጠት ብዙ ምንዳ እንዳገኙት እነርሱ ግን በድህነታቸው ምክንያት ይህን ብዙ ምንዳ ለማግኘት ሶደቃ መስጠት እንዳልቻሉና እንደነርሱ ብዙ መልካም ምንዳ የሚያገኙበትን መፍትሄ ፍለጋ ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስሞታ አቀረቡ፡ ሀብታሞቹ እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ፤ እንደምንጾመውም ይጾማሉ፤ ሀብታሞች በትርፍ ገንዘቦቻቸው ምፅዋት ሲሰጡ እኛ ግን ምፅዋት አንሰጥም። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሊያደርጉት የሚችሉትን ሶደቃ በመጠቆም እንዲህ አሏቸው: "በራሳቹ ላይ የምትመፀውቱትን ነገር አላህ አላደረገላችሁምን? (ሱብሓነሏህ/ ጥራት ለአላህ የተገባው ነው) በማለታችሁ ለናንተ የሶደቃ ምንዳ ያስገኝላችኋል፤ ልክ እንደዚሁ (አሏሁ አክበር/ አላህ ታላቅ ነው) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ (አልሐምዱሊላህ/ ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ (ላኢላሃ ኢለሏህ/ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከዚህም በላይ ሚስታችሁን መገናኘታችሁ ራሱ ሶደቃ ነው።" ሶሐቦችም ተገርመው "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን ስሜቱን ስላስደሰተ በርሷ ምንዳ ይኖረዋልን?" አሉ። እርሳቸውም "ንገሩኝ እስኪ ብልቱን ዝሙት ላይ ወይም ከዛ ውጪ በሆነ ክልክል ቦታ ላይ ቢያኖራት በርሱ ላይ ወንጀለኝነት አይኖርበትምን? ልክ እንደዚሁ የሚፈቀድለት ቦታ ላይ ካኖራት ደሞ ምንዳ ይኖረዋል።" አሉ።فوائد الحديث
ሶሐቦች በመልካም ተግባር ላይ ያላቸው እሽቅድድምና ትልቅ ምንዳን ለማግኘትና አላህ ዘንድ ያለውን ትሩፋት ለማግኘት ጥረት እንደሚያደርጉ እንረዳለን።
የመልካም ተግባራት መንገዶች ብዙ እንደሆኑና አንድ ሙስሊም በመልካም ኒያና በጥሩ አላማ የሚሰራውን ስራ ሁሉ እንደሚያካትት እንረዳለን።
የእስልምና ገርነትና ቀላልነትን እንረዳለን። ሁሉም ሙስሊም አላህን ለመገዛት አስቦ የሚሰራውን ስራ እንደየራሱ አለለት።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የሚፈቀዱ ነገሮች እውነተኛ ኒያ ተነይቶባቸው ከተሰሩ አምልኮ እንደሚሆኑ ማስረጃ ይሆናል። ግንኙነት ማድረግ የሚስትን ሐቅ ለመወጣት፤ አላህ ባዘዘው መልኩ በመልካም መኗኗር ተነይቶበት ወይም መልካም ልጅ ተፈልጎበት ወይም ነፍሱን ከዝሙት ለማቀብ ብሎ ወይም ሚስቱን ከዝሙት ለማቀብ ብሎና ወደ ሐራም ከመመልከት ወይም ስለርሱ ከማሰብ ወይም ስለርሱ ከማብሰልሰል ለመታቀብ ብሎ ወይም ከዚህ ውጪ ላሉ መልካም አላማዎች ነይቶበት ከሆነ የሚያደርገው አምልኮ ይሆንለታል።"
ሰሚው ነፍስ ውስጥ ዘልቆ እንዲገባና ግልፅ እንዲሆን ምሳሌና ቂያስን ማድረግ እንደሚገባ እንረዳለን።