إعدادات العرض
አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ) አሁንም አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ) አሁንም አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ)" "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማንን ነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ከወላጆቹ…
አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ) አሁንም አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ) አሁንም አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ)" "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማንን ነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ከወላጆቹ ሁለቱን ወይም አንዱን በእርጅና ወቅት አግኝቷቸው ጀነት ያልገባ ነው።" አሉ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ) አሁንም አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ) አሁንም አፍንጫው በአፈር ትታሽ (ይዋረድ)" "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማንን ነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ከወላጆቹ ሁለቱን ወይም አንዱን በእርጅና ወቅት አግኝቷቸው ጀነት ያልገባ ነው።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Hausa Kurdî Kiswahili Português தமிழ் دری অসমীয়া Svenska ไทย Yorùbá Кыргызча ગુજરાતી नेपाली Română മലയാളം Nederlands Oromoo తెలుగు پښتو Soomaali Kinyarwanda Malagasy ಕನ್ನಡ Српски Moore ქართულიالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዱዓቸውን ጥግ ከማድረሳቸው የተነሳ አፍንጫውን አፈር ላይ እንደተደፋ ሰው በማድረግ በውርደት እንዲከናነብ ሶስት ጊዜ ረገሙት። የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማንን ነው የረገሙት? ተብለው ተጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዳቸውን ወይም ሁለቱን ወላጆቹ በእርጅና ወቅት አግኝቶ እነርሱ ጀነት ለመግባቱ ሰበብ ያልሆኑት ነው አሉ። ይህም የሚሆነው ለነርሱ በጎ ባለማድረጉና ሐቃቸውን በመንፈጉ ምክንያት ነው።فوائد الحديث
ለወላጆች በጎ ማድረግ በተለይ ባረጁና በደከሙ ወቅት ግዴታ መሆኑንና ከጀነት መግቢያ ሰበቦች መካከል አንዱ እንደሆነ እንረዳለን።
የወላጆችን ሐቅ ማጓደል ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።
التصنيفات
ለወላጆች መልካም የመዋል ትሩፋቶች