إعدادات العرض
አንዳችሁ ወደ ቤተሰቡ የተመለሰ ጊዜ ሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎችን ቢያገኝ ያስደስተዋልን?
አንዳችሁ ወደ ቤተሰቡ የተመለሰ ጊዜ ሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎችን ቢያገኝ ያስደስተዋልን?
አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦ "አንዳችሁ ወደ ቤተሰቡ የተመለሰ ጊዜ ሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎችን ቢያገኝ ያስደስተዋልን?" እኛም "አዎን" አልን። እሳቸውም "አንዳችሁ በሰላቱ ውስጥ የሚያነባቸው ሶስት አንቀፆች ከሶስት ትላልቅ የሰቡ እርጉዝ ግመሎች ለሱ የተሻሉ ናቸው።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
ar en my sv cs gu yo nl ur es id ug bn tr bs si hi vi ha ml te sw ps as sq prs el bg ff kn ky lt ro rw sr tg uz ne ku mos so wo fr tl uk az ta bm de ka pt mk hu ru zh fa km mg omالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰላት ውስጥ ሶስት አንቀፆችን በማንበብ የሚገኘው ምንዳ አንድ ሰው ቤቱ ውስጥ ሶስት የሰቡ ትላልቅ እርጉዝ ግመሎችን ከሚያገኝ እንደሚበልጥ ገለፁ።فوائد الحديث
ሰላት ውስጥ ቁርኣን የማንበብ ትሩፋት መገለፁ።
መልካም ሥራዎች ከጠፊዋ ዱንያ መጣቀሚያ የተሻሉና ዘውታሪዎች ናቸው።
ይህ ትሩፋት ሦስት አንቀፆችን በማንበብ ብቻ የተገደበ አይደለም። ሰጋጁ ሰላቱ ውስጥ የሚያነባቸውን አንቀፆች በጨመረ ቁጥር የሚያገኘው ምንዳ ለሱ በሚያነባቸው ቁጥር ልክ የእርጉዝ ግመሎች ከሚሰጠው የተሻለ ነው።
التصنيفات
የተከበረው ቁርአን ትሩፋቶች