إعدادات العرض
ዕውቀትን ዑለሞችን ልትፎካከሩበት (በሊቃውንት ፊት ለመታየት)፣ ቂሎችን ልትሟገቱበት
ዕውቀትን ዑለሞችን ልትፎካከሩበት (በሊቃውንት ፊት ለመታየት)፣ ቂሎችን ልትሟገቱበት
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "ዕውቀትን ዑለሞችን ልትፎካከሩበት (በሊቃውንት ፊት ለመታየት)፣ ቂሎችን ልትሟገቱበት፣ በመድረኮች ላይ ቅድሚያ እንድትመረጡበት በማለም እንዳትቀስሙ። ይህን የፈፀመ (ለርሱ) እሳት አለው እሳት አለው።"
[ሶሒሕ ነው።] [ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية English မြန်မာ Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Español Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe Bosanski සිංහල हिन्दी Tiếng Việt Hausa മലയാളം తెలుగు Kiswahili پښتو অসমীয়া Shqip دری Ελληνικά Български Fulfulde ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek नेपाली Kurdî Wolof Moore Soomaali Français Azərbaycan Tagalog Українська தமிழ் bm Deutsch ქართული Português Македонски Magyar Русский 中文 فارسی ភាសាខ្មែរ Malagasy Oromooالشرح
ዑለሞችን ለመወዳደርና ለመፎካከር፣ እኔ እንደናንተው ዓሊም ነኝ የሚለውን ለማሳየት ወይም ቂሎችንና ደካማ ግንዛቤ ያላቸውን ልትሟገቱና ልታናግሩ ወይም በመድረኮች ግንባር ቀደም ለመሆንና ከሌላው ቅድሚያ እንዲሰጠው በማለም ዕውቀት ከመፈለግ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አስጠነቀቁ። ይህን የፈፀመ ሰው፤ ለአላህ ብሎ ዕውቀት በመፈለግ ላይ እሱ ለይዩልኝና ያለ ኢኽላስ በመስራቱ እሳት ይገባዋል።فوائد الحديث
ዕውቀትን ሊፎካከርበት ወይም ሊሟገትበት ወይም በመድረኮች ቅድሚያ እንዲሰጠውና ለመሳሰሉት አላማዎች የተማረ ሰው በእሳት እንደተዛተበት እንረዳለን።
ዕውቀትን ለሚማርና ለሚያስተምር ሰው ኒያን ማጥራት አንገብጋቢ ነው።
ኒያ የሥራ መሰረት መሆኑንና ምንዳም በኒያ ላይ የተመረኮዘ መሆኑን ተረድተናል።