አላህ የቀጥተኛውን መንገድ ምሳሌ አደረገ

አላህ የቀጥተኛውን መንገድ ምሳሌ አደረገ

ከነዋስ ቢን ሰምዓን አል'አንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ የቀጥተኛውን መንገድ ምሳሌ አደረገ። በቀጥተኛው መንገድ ዳርና ዳር ሁለት አጥር (ግድግዳ) አሉ፤ አጥሮቹ ዘንድ የተከፈቱ በሮች ይገኛሉ፤ በሮቹ ላይም የተለቀቁ መጋረጃዎች አሉ፤ በመንገዱ በር ላይ "ሰዎች ሆይ! ሁላቹም ወደቀጥተኛው መንገድ ግቡ እንዳትጣመሙ!" የሚል ተጣሪ አለ። ከቀጥተኛው መንገድ ከላይ ሆኖ የሚለፍፍ አንድ ተጣሪ አለ ፤ ከነዛ በሮች አንዱን መክፈት የፈለገ ጊዜ "ወዮልህ እንዳትከፍተው! ከከፈትከው ትገባለህ!" ይለዋል። ቀጥተኛው መንገድ ኢስላም ነው፤ ሁለቱ አጥሮች የአላህ ድንበሮች ናቸው፤ የተከፈቱት በሮች የአላህ ክልከላዎች ናቸው፤ ከቀጥተኛው መንገድ አናት ላይ የሚጣራው የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከቀጥተኛው መንገድ ከላይ ሆኖ የሚጣራው በሁሉም ሙስሊም ቀልብ ውስጥ የሚገኝ የአላህ መካሪ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

الشرح

አላህ ኢስላምን ምንም ሳይጣመም በተዘረጋ ቀጥተኛ መንገድ መሰለው፤ በዚህ መንገድ ዳርና ዳር ሁለት ዙሪያውን የከበቡት አጥሮች አሉ እነሱም የአላህ ድንበሮች ናቸው፤ እነዚህ ሁለት አጥሮች የተከፈቱ በሮች ሲኖራቸው እነሱም የአላህ ክልከላዎች ናቸው፤ በመንገዱ የሚያልፍ ሰው በበሩ ውስጥ የሚገኘው ግልፅ እንዳይሆንለት በነዚህ በሮች ላይ የተዘጋጀ መጋረጃ አለ፤ በመንገዱ መነሻ ሰዎችን "መንገዳችሁን ወደጎንና ጎን ሳትዘነበሉ ቀጥ ብላችሁ ሂዱ!" እያለ የሚጠቁምና የሚመራ ተጣሪ አለ። ይህ ተጣሪም የአላህ መጽሐፍ ነው፤ እዚህ ቦታ ላይ የመንገዱ አናት ላይ ሆኖ የሚጣራ ሌላ ተጣሪም አለ፤ ይህ ተጣሪ መንገደኛው እነዛን የበሮቹ መጋረጃ ትንሽ ለመክፈት ባሰበ ቁጥር "ወዮልህ እንዳትከፍተው! መጋረጃውን ከከፈትከው ነፍስህን ውስጡ እንዳትገባ መቆጣጠር ስለማትችል ትገባለህ!" እያለ የሚያስጠነቅቀው ነው። ይህ ተጣሪም በሁሉም ሙስሊም ቀልብ ውስጥ የሚገኝ የአላህ መካሪ ነው። በማለት ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የምሳሌውን ፍቺ አብራሩት።

فوائد الحديث

ኢስላም እውነተኛ ሃይማኖትና ወደ ጀነት የሚያደርሰን ቀጥተኛ መንገድ ነው።

የአላህን ድንበሮች ሐላልና ሐራም ባደረጋቸው ጉዳዮች አጥብቆ መያዝ ግዴታ መሆኑና በነዚህ ላይ መዘናጋት ለጥፋት እንደሚዳርግ እንረዳለን።

የታላቁን ቁርኣን ደረጃና እርሱን መተግበር መበረታታቱ፤ በውስጡ መመሪያ፣ ብርሃንና ስኬትን ይዟል።

አላህ በአማኞች ቀልብ ውስጥ ጥፋት ላይ ከመውደቅ የሚከለክላቸውና የሚገስፃቸውን ማኖሩ በባሮቹ ላይ ያለውን እዝነት ያሳያል።

አላህ በእዝነቱ ለባሮቹ ወንጀል ውስጥ ከመውደቅ የሚከለክላቸው አስጠንቃቂዎች ማድረጉን ተረድተናል።

ከማስተማር መንገዶች መካከል ትምህርቱ ግልፅና ለመረዳት ቅርብ እንዲሆን ምሳሌ መጥቀስ አንዱ እንደሆነ ተረድተናል።

التصنيفات

የተከበረው ቁርአን ትሩፋቶች, የቀልብ ተግባራት, ከዝንባሌና ስሜት ማውገዝ