የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት ይገቡና እኔና የኔ እኩያ የሆነ ልጅም ውሃ የያዘ ዕቃና አንካሴ ተሸክመን እንወስድላቸው ነበር። በውሃውም…

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት ይገቡና እኔና የኔ እኩያ የሆነ ልጅም ውሃ የያዘ ዕቃና አንካሴ ተሸክመን እንወስድላቸው ነበር። በውሃውም እስቲንጃእ ያደርጉበት ነበር።

ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት ይገቡና እኔና የኔ እኩያ የሆነ ልጅም ውሃ የያዘ ዕቃና አንካሴ ተሸክመን እንወስድላቸው ነበር። በውሃውም እስቲንጃእ ያደርጉበት ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እርሱና የርሱ እኩያ የሆነ ሌላ አገልጋይ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ መፀዳጃ ቤት በሚሄዱበት ወቅት ይከተሏቸው እንደነበረና ከራሳቸው ጋርም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲፀዳዱ እርሱ ላይ አንድ ነገር አንጠልጥለው የሚከልሉበት ወይም ለሶላታቸው መከለያ የሚያደርጉት እንደጦር ጫፍ አምሳያ ጫፉ ላይ ሹልነት ያለውን ዘንግ እንደሚሸከሙ፤ በተጨማሪም ከቆዳ በተሰራ ትንሽዬ የውሃ መያዣ ውሃ ሞልተው ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደሚወስዱ ተናገረ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተፀዳድተው ሲጨርሱም ከሁለቱ አንዱ ውሃን ያቀብላቸውና በውሃው ኢስቲንጃእ እንደሚያደርጉ ተናገሩ።

فوائد الحديث

አንድ ሙስሊም በሚፀዳዳ ወቅት ለመታጠብ ሲቆም ነጃሳው እንዳያጨመላልቀው የሚታጠብበትን ውሃ ቀድሞ ማዘጋጀት እንዳለበት እንረዳለን።

በሚፀዳዳበት ጊዜ ሀፍረተ ገላውን ማንም ሰው እንዳያይበት መደበቅ ይገባል። ምክንያቱም የሌላን ሰው ሀፍረተ ገላ መመልከት ክልክል ነው። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) መሬት ላይ አንካሴያቸውን ተክለው የሚሸፍናቸውን ልብስ አንካሴው ላይ ያደርጉ ነበር።

ልጆች ኢስላማዊ ስነ-ስርዓትን እንዲወርሱ ማስተማርና በዛም ላይ ማነፅ እንደሚገባ እንረዳለን።

التصنيفات

የሶሐቦች (ረዺየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ትሩፋቶች, የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አገልጋዮች, ነጃሳን ማስወገድ, የመፀዳጃ ቤት ስነ-ስርዓት, ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመፀዳዳት ወቅት የነበራቸው መመሪያ