إعدادات العرض
'ዱዓእ እሱ አምልኮ ነው።
'ዱዓእ እሱ አምልኮ ነው።
ከኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: 'ዱዓእ እሱ አምልኮ ነው።' ከዚያም {ጌታችሁም አለ "ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።"} [ጋፊር: 60] የሚለውን አነበቡ።"
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية తెలుగు हिन्दी Kurdî English Kiswahili Français فارسی தமிழ் සිංහල မြန်မာ Русский ไทย Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands اردو Bahasa Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Türkçe Bosanski Hausa മലയാളം دری Fulfulde Magyar ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски O‘zbek Moore नेपाली Oromoo Wolof Български Українська Português Tagalog Azərbaycan ქართული тоҷикӣ Македонски bm 中文 Malagasyالشرح
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱዓእ አምልኮ እንደሆነ ተናገሩ። በዱንያና በአኺራዊ ጉዳዮች የሚጠቅመውን ነገር እንዲሰጠውና የሚጎዳውን ነገር እንዲከላከልለት አላህ የሚጠየቅበት ልመናዊ ዱዓም ይሁን፤ ማንኛውም ውጫዊና ውስጣዊ ንግግርም ተግባርም አላህ የሚወዳቸውና የሚያስደስተው ልባዊ፣ አካላዊና ገንዘባዊ አምልኮዎችን የሚያደርጉበት አምልኳዊ ዱዓእም ያው ነው። እነዚህ የዱዓእ አይነቶችም ለአላህ ብቻ ጥርት ተደርገው መፈፀማቸው ግዴታ ነው። ከዚያም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለዚህ ንግግራቸው የአላህን ንግግር ማስረጃ አደረጉ። አላህ እንዲህ ብሏል፦ {ጌታችሁም አለ "ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።"}فوائد الحديث
ዱዓእ የአምልኮ መሰረት በመሆኑ ከአላህ ውጪ ለሆነ መስጠት አይፈቀድም።
ዱዓእ እውነተኛ ባርነትን፣ የጌታን መብቃቃትና ችሎታ እውቅና መስጠትን እና የባሪያን ወደ አላህ ፈላጊነቱን ያካተተ ነው።
ከአላህ አምልኮ በመኩራትና ዱዓእን በመተው ምንዳ ዙሪያ ብርቱ ዛቻ መምጣቱን እንረዳለን። አላህን ከመለመን የሚኮሩ ሰዎች ጀሀነም የተናነሱና የተዋረዱ ሆነው ይገባሉ።
التصنيفات
የዱዓእ ትሩፋቶች