በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ "ጥራት ምስጋና ለአላህ ይገባው።" ያለ ሰው (የወንጀሉ ብዛት) የባህር ዓረፋ አምሳያ ቢሆን እንኳ ወንጀሉ ይታበስለታል።

በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ "ጥራት ምስጋና ለአላህ ይገባው።" ያለ ሰው (የወንጀሉ ብዛት) የባህር ዓረፋ አምሳያ ቢሆን እንኳ ወንጀሉ ይታበስለታል።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ "ጥራት ምስጋና ለአላህ ይገባው።" ያለ ሰው (የወንጀሉ ብዛት) የባህር ዓረፋ አምሳያ ቢሆን እንኳ ወንጀሉ ይታበስለታል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ "ሱብሓነሏሂ ወቢሐምዲሂ" (ጥራት ምስጋና ለአላህ ይገባው።) ያለ ሰው ባህር በሚናወጥ ወቅት ከላዩ እንደሚንጣለለው ነጭ አረፋ አምሳያ ወንጀሉ የበዛ ቢሆን እንኳ ወንጀሉ ይማራል ይታበሳል ብለው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እየተናገሩ ነው።

فوائد الحديث

ይህን ምንዳ የሚያገኘው በቀን ውስጥ አከታትሎም ይሁን በተለያየ ጊዜ እነዚህን ቃላት ያለ ሰው ነው።

ተስቢሕ ማለት: - አላህን ከጉድለት ማጥራት ሲሆን ፤ ሐምድ ማለት ደግሞ አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በምሉዕነት መግለፅ ነው።

በሐዲሡ ወንጀልን ማስማር ከሚለው የተፈለገበት ትናንሽ ወንጀሎችን ብቻ ነው። ትላልቅ ወንጀሎች ግን የግድ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።

التصنيفات

የዚክር ትሩፋቶች