ሐላል (የተፈቀደ) ነግር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነግር ሁሉ ግልፅ ነው።

ሐላል (የተፈቀደ) ነግር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነግር ሁሉ ግልፅ ነው።

ከኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: -ኑዕማን (መስማቱን ለማረጋገጥ) በሁለት ጣቶቹ ወደ ጆሮዎቹ እየጠቆመ፦ "ሐላል (የተፈቀደ) ነግር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነግር ሁሉ ግልፅ ነው። በመካከላቸው አብዛኛው ሰዎች የማያውቃቸው አሻሚ ጉዳዮች አሉ። አሻሚ ጉዳዮችን የተጠነቀቀ ሰው ሃይማኖቱንና ክብሩን ጠብቋል። አሻሚ ጉዳዮች ላይ የወደቀም ሰው ሐራም ላይ ወድቋል። የዚህ ሰው አምሳያ ልክ የተከለከለ ክልል ወሰን ዙሪያ እንደሚጠብቅና እንስሳዎቹም ወሰን አልፈው የሰው እርሻ ሊገቡ እንደቀረቡበት እረኛ ነው። አዋጅ! ለሁሉም ንጉስ ወሰን (ድንበር) አለው። አዋጅ! የአላህ ወሰን (ድንበር) ደግሞ ክልከላው ነው። አዋጅ! ሰውነት ውስጥ የምትገኝ ቁራጭ ስጋ አለች። እሷ ከተስተካከለች ሁሉም ሰውነት ይስተካከላል። እሷ ከተበላሸች ደግሞ ሁሉም ሰውነት ይበላሻል። አዋጅ! እሷም ልብ ናት።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለነገሮች ሁሉ የሚያገለግል አጠቃላይ መርህን እያብራሩ ነው። ነገሮች ሁሉ በሸሪዐ መሰረት ወደ ሶስት ክፍሎች ይከፈላሉ: ግልፅ ሐላል ፣ ግልፅ ሐራምና ከፍቁድነትና ክልክልነት አንፃር ብዙ ሰው ብይናቸውን የማያውቃቸው ግልፅ ያልሆኑ አሻሚ ጉዳዮች ናቸው። በሱ ላይ አሻሚ የሆኑበትን ጉዳዮች የተወ ሰው ሀራም ላይ ከመውደቅ በመራቁ ሳቢያ እምነቱ ሰላም ይሆናል፤ ይህን አሻሚ የሆነ ጉዳይ በመፈፀሙ ሳቢያ እሱ ላይ የሚደርስን የሰዎች ትችት ስለማይኖርም ክብሩ ከትችት ሰላም ይሆናል። አሻሚ ጉዳዮችን ያልራቀ ሰው ግን ወይ ሐራም ላይ በመውደቅ ወይ በሰዎች ክብሩ በመዘለፉ ሳቢያ ነፍሱን (ለችግር) ያጋልጣታል። መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አሻሚ ጉዳዮች የሚፈፅምን ሰው ሁኔታ ለማብራራት ምሳሌ ጠቀሱ። እሱም ልክ ባለቤቱ በከለላት ስፍራ አስጠግቶ ከብቶቹን እንደሚያሰማራ እረኛ ነው። ቀስ በቀስ የእረኛው ከብቶች ወደተከለለው ስፍራ ቅርብ ስለሆኑ ክልሉ ውስጥ ዘልቀው ሊበሉ ይቀርባሉ። ልክ እንደዚሁ አሻሚ የሆኑ ጉዳዮችን የሚሰራ ሰው በዚህ መዳፈሩ ሳቢያ ወደ ሐራም ይቃረባል። ቀስበቀስ ሐራም ውስጥ ሊወድቅም ይቀርባል። ቀጥለውም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰውነት ውስጥ የምትገኝ ቁራጭ ስጋ እንዳለች ገለፁ። (እሷም ልብ ናት።) በሷ መስተካከል ሰውነት ይስተካከላል በሷ መበላሸትም ሰውነት ይበላሻል።

فوائد الحديث

ብይናቸው ግልፅ ያልሆኑ አሻሚ ጉዳዮችን መተው መበረታታቱ።

التصنيفات

ሸሪዓዊ ፍርድ, ሸሪዓዊ ፍርድ, የቀልብ ተግባራት ትሩፋቶች, የቀልብ ተግባራት ትሩፋቶች, ነፍስን ማጥራት, ነፍስን ማጥራት