إعدادات العرض
አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: "ደጋግ ለሆኑ ባሪያዎቼ ዓይን ያላየችው፤ ጆሮ ያልሰማችው፤ በሰው ቀልብ ላይ ውል ያላለን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።"»
አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: "ደጋግ ለሆኑ ባሪያዎቼ ዓይን ያላየችው፤ ጆሮ ያልሰማችው፤ በሰው ቀልብ ላይ ውል ያላለን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።"»
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ «አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: "ደጋግ ለሆኑ ባሪያዎቼ ዓይን ያላየችው፤ ጆሮ ያልሰማችው፤ በሰው ቀልብ ላይ ውል ያላለን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።"» «አቡ ሁረይራም እንዲህ አለ: "ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ {ይሰሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለነርሱ የተደበቀላቸውን (ፀጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም።} [አስሰጅዳ:17]"»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Tiếng Việt অসমীয়া Nederlands Kiswahili Hausa සිංහල ไทยالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ማለቱን ተናገሩ: "ደጋግ ባሪያዎቼን ጀነት ውስጥ ለማላቅ ስለርሱ ምንነት አይን ያላየችውን፤ ስለርሱ ባህሪ ጆሮ ያልሰማችውን፤ ስለእውነተኛ ሁኔታዋ በሰው ቀልብ ላይ ውል ብሎ ያላለፈና ያልተከሰተን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።" አቡ ሁረይራም (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: "ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ: {ይሰሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለነርሱ የተደበቀላቸውን (ፀጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም።}" [አስሰጅዳ:17]فوائد الحديث
ይህ ሐዲሥ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከጌታቸው ከሚያስተላልፉት ሐዲሥ መካከል አንዱ ነው። ሐዲሠል ቁድሲይ ወይም ሐዲሠል ኢላሂይ በመባልም ይጠራል። ቃሉም ሀሳቡም ከአላህ ሲሆን ነገር ግን ቁርአን ከሌሎች የተለየበት የሆኑ ማንበቡ ብቻ (በየፊደላቱ ሐሰና የሚያስገኘውን) አምልኮ መሆን፤ እሱን ለማንበብ ውዱእ ማድረግና አምሳያውን ማንም እንደማያመጣ መነገሩ፤ መሰረታዊ ተአምራዊነቱና ከዚህም ውጪ ያሉ የቁርአን መለዮዎችን አልያዘም።
አላህ ለደጋግ ባሮቹ ያዘጋጀውን ለመጎናፀፍ ትእዛዛትን በመፈፀም ላይና ውግዝ ተግባራትን በመተው ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
አላህ በቁርአን ውስጥም ይሁን በመልክተኛው ሱንና ጀነት ውስጥ የሚገኘውን ሁሉንም ፀጋ አላሳወቀንም። ስለ ጀነት ከምናውቀው ይልቅ የማናውቀው ይበልጣል።
የጀነት ፀጋ የተሟላ መሆኑ መገለፁ፤ ነዋሪዎቿም ከደፈረሰ ወይም ፍርሃት ከተሞላበት ህይወት የራቀ መደሰቻዎችን ያገኛሉ።
የዱንያ መጣቀሚያ ጠፊ ሲሆን የመጪው አለም ህይወት ደግሞ የተሻለና ቀሪ ነው።
التصنيفات
የጀነትና እሳት ባህሪዎች