ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት - الصفحة 3

ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት - الصفحة 3

48- አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነልዐጅዚ ወልከሰሊ ወልጁብኒ ወልቡኽሊ ወልሀረሚ ወዐዛቢል ቀብር ፤ አልሏሁምመ አቲ ነፍሲ ተቅዋሃ ወዘክኪሃ አንተ ኸይሩ መን ዘክካሃ፤ አንተ ወሊይዩሃ ወመውላሃ፤ አልሏሁምመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዒልሚን ላ የንፈዑ፤ ወሚን ቀልቢን ላ የኽሸዑ፤ ወሚን ነፍሲን ላ ተሽበዑ፤ ወሚን ደዕወቲን ላ ዩስተጃቡ ለሃ።" (ትርጉሙም፡ "አላህ ሆይ! እኔ ከስንፍና ፣ ከመታከት ፣ ከፈሪነት ፣ ከስስት ፣ ከመጃጀትና ከቀብር ቅጣት ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ለነፍሴ ፍራቻዋን ስጣት፤ ነፍሴን ለማጥራት የተሻልከው አንተው ነህና ነፍሴን አጥራት፤ አንተ ረዳቷና ተቆጣጣሪዋ ነህና። አላህ ሆይ! እኔ ከማይጠቅም ዕውቀት፣ አንተን ከማይፈራ ልብ፣ ከማትጠግብ ነፍስ፣ ተቀባይነት ከሌላት ዱዓም ባንተ እጠበቃለሁ።")