ሰዎች አላህን ያላወሱበትና በነቢያቸው ላይ ሶላት ያላወረዱበት መቀማመጥ ከተቀመጡ በነርሱ ላይ ቁጭት ይሆንባቸዋል። ከፈለገ ይቀጣቸዋል ከፈለገም ይምራቸዋል።

ሰዎች አላህን ያላወሱበትና በነቢያቸው ላይ ሶላት ያላወረዱበት መቀማመጥ ከተቀመጡ በነርሱ ላይ ቁጭት ይሆንባቸዋል። ከፈለገ ይቀጣቸዋል ከፈለገም ይምራቸዋል።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሰዎች አላህን ያላወሱበትና በነቢያቸው ላይ ሶላት ያላወረዱበት መቀማመጥ ከተቀመጡ በነርሱ ላይ ቁጭት ይሆንባቸዋል። ከፈለገ ይቀጣቸዋል ከፈለገም ይምራቸዋል።"

[ሶሒሕ ነው።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህን ከማውሳት ከመዘናጋት አስጠነቀቁ። እርሱም ሰዎች አላህን በርሱ ያላወሱበትና በመልክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶላት ያላወረዱበት መቀማመጥ ከተቀመጡ ይህ መቀማመጥ የትንሳኤ ቀን በነርሱ ላይ ቁጭት፣ ፀፀት፣ ክስረትና ጉድለት ይሆንባቸዋል። ከፈለገ አላህ በቀደመ ወንጀላቸውና ባለባቸው ጉድለት ምክንያት ይቀጣቸዋል። ከፈለገም በችሮታውና በእዝነቱ ለነርሱ ይምራቸዋል።

فوائد الحديث

በዚክር ላይ መነሳሳቱና ትሩፋቱ መገለፁን ተረድተናል።

አላህና መልክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሚወሱበት ቦታ ላይ መቀማመጥ ትሩፋት እንዳለው፤ ይህ የሌለበት መቀማመጥ ደግሞ በሰዎቹ ላይ የትንሳኤ ቀን የእድለቢሶች መቀማመጥ እንደሆነ እንረዳለን።

አላህን ከማውሳት ከመዘናጋት የመጣው ክልከላ በመቀማመጥ ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም። ይልቁንም ሌሎችንም ሁኔታዎች ያጠቃልላል። ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "አንድ ስፍራ ላይ የተቀመጠ ሰው አላህን ከማውሳቱ በፊት ያንን ስፍራ መለየቱ ይጠላል።"

የትንሳኤ ቀን የሚያጋጥማቸው ቁጭት ወይ ወቅቱን አላህን በመገዛት ስላልተጠቀሙበት ምንዳና አጅር ስላመለጣቸው ነው፤ ወይም ደግሞ ወቅቱን በወንጀል በማሳለፋቸው ስለተጠመዱ በሚያጋጥማቸው ወንጀልና ቅጣት ነው።

መዘናጋቱ የሚፈቀዱ ነገሮች ላይ በመጠመድ ምክንያት ለሆነ ሰው ይህ ማስጠንቀቂያ ከመጣ ሀሜት፣ ሰውና ሰውን ማጣላትንና የመሳሰሉትን ክልክል ነገሮች ባካተተ ስብስቦች ላይ ተጠምዶ የተዛናጋስ ወንጀሉ እንዴት ይሆን?

التصنيفات

ልቅ የሆኑ ዚክሮች