إعدادات العرض
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠቅለል ያሉ ዱዓዎችን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለውንም ይተዉ ነበር።
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠቅለል ያሉ ዱዓዎችን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለውንም ይተዉ ነበር።
ከምእመናን እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠቅለል ያሉ ዱዓዎችን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለውንም ይተዉ ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Português සිංහල Русский Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી Nederlands മലയാളം Românăالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የዱንያንም ሆነ የመጪውን አለም መልካም ነገር የጠቀለለ አላህ ላይ ማወደስና መልካም ፍላጎቶችንም ያካተተ ሁኖ ቃሉ አንሶ ሀሳቡ የበዛ ዱዓን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለንም ይተዉ ነበር።فوائد الحديث
ዱዓን በጥቂትና በርካታ ሀሳቦችን በሰበሰቡ ቃላቶች ማድረግ እንደሚወደድ፤ ዱዓ ላይ የቃላት ስንጠቃና ከአቅም በላይ መጣጣርም እንደሚጠላ የነቢዩንም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መመሪያ መቃረን ነው።
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በጠቅላይ ቃላቶች ተለይተዋል።
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዱዓ እንዳደረጉበት የተረጋገጡ ዱዓዎች ላይ ቢረዝምና ቃሉ ቢበዛ እንኳ ያንን ዱዓ ማድረግ ላይ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ተረድተናል።
التصنيفات
የዱዓእ ስነ-ስርዓት