إعدادات العرض
1- ወንጀልም ሆነ ዝምድና መቁረጥ የሌለበትን ዱዓ የሚያደርግ አንድም ሙስሊም የለም በዛች ዱዓው ምክንያት አላህ ከሶስት ነገሮች አንዱን የሚሰጠው ቢሆን እንጂ: ወይ የለመነው በፍጥነት ይሰጠዋል ፤ ወይ ልመናው ለመጪው ዓለም መልካም ምንዳ ማደለቢያ ይሆንለታል፤ ወይም የለመነውን ጉዳይ የሚያክል መጥፎ ነገር ከሱ ዞር ያስደርግለታል። " ሶሀቦችም " ስለዚህ (ዱዓእ) እናብዛ?" አሉ። እሳቸውም "(ዱዓእ ካበዛችሁ) የአላህ ስጦታም እጅግ ይበዛል።" አሏቸው።
2- ጌታችሁ የሚያፍርና ቸር ነው። ባሪያው የልመና እጆቹን ወደርሱ ከፍ አድርጎ ለምኖት በባዶ መመለስን ያፍራል።
3- የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠቅለል ያሉ ዱዓዎችን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለውንም ይተዉ ነበር።
4- አንዳችሁ አላህ ሆይ! ከፈለግክ ማረኝ! ከፈለግክ እዘንልኝ! ከፈለግክ ሲሳይን ለግሰኝ! አይበል። ጥያቄውን ቁርጥ ያድርግ። እርሱ አላህ የሻውን ይሰራልና። ለርሱም አስገዳጅ የለውም።