إعدادات العرض
ጌታችሁ የሚያፍርና ቸር ነው። ባሪያው የልመና እጆቹን ወደርሱ ከፍ አድርጎ ለምኖት በባዶ መመለስን ያፍራል።
ጌታችሁ የሚያፍርና ቸር ነው። ባሪያው የልመና እጆቹን ወደርሱ ከፍ አድርጎ ለምኖት በባዶ መመለስን ያፍራል።
ከሰልማን - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጌታችሁ የሚያፍርና ቸር ነው። ባሪያው የልመና እጆቹን ወደርሱ ከፍ አድርጎ ለምኖት በባዶ መመለስን ያፍራል።"»
[ሐሰን ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Hausa Kurdî Português தமிழ் Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી Nederlands മലയാളം Românăالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዱዓእ ስናደርግ እጅን ከፍ በማድረግ ላይ አነሳሱ። አላህ (ሐይዩን) እጅግ በጣም የሚያፍር፤ መስጠትን የማይተው፤ ለባሪያው የሚያስደስተውን የሚያደርግና የሚጎዳውን የሚያስቀርለት ነው። (ከሪሙን) ሳይጠየቅ የሚሰጥ ቸር ነው። ከተጠየቀ በኋላስ (እንዴት ሊመልሰው ይሆን)?! አማኝ ባሪያው ለዱዓ ሁለት እጆቹን አንስቶ ለምኖት ለርሱ ባዶ አድርጎ መመለስን ያፍራል።فوائد الحديث
የሰው ልጅ ወደ አላህ ፈላጊነቱንና ባርነቱን ግልፅ ባደረገ ቁጥር ዱዓው ተቀባይነት ማግኘቱም ተስፋ የሚደረግና ቅርብ ይሆናል።
ዱዓእ በማድረግ መነሳሳቱን፣ እጆችን ማንሳት ተወዳጅ እንደሆነና እጆችን ማንሳት የዱዓ ተቀባይነትን ከሚያስገኙ ምክንያቶች መካከል አንዱ መሆኑን እንረዳለን።
አላህ ለባሮቹ ያለው ቸርነትና እዝነት ስፋቱ መገለፁን ተረድተናል።
التصنيفات
የዱዓእ ስነ-ስርዓት