ምግብ ስትበሉ ተሰብሰቡ። (አንድ ላይ ብሉ) የአላህንም ስም በምግባቹ ላይ አውሱ። አላህ ምግባችሁን ይባርክላችኋል።

ምግብ ስትበሉ ተሰብሰቡ። (አንድ ላይ ብሉ) የአላህንም ስም በምግባቹ ላይ አውሱ። አላህ ምግባችሁን ይባርክላችኋል።

ከወሕሺይ ቢን ሐርብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: «እነርሱ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ እየበላን አንጠግብም።" አሏቸው። እርሳቸውም "ምናልባት ተበታትናችሁ ለየብቻ እየበላችሁ ይሆን?" ብለው ጠየቋቸው። እነርሱም "አዎን" አሉ። እርሳቸውም "ምግብ ስትበሉ ተሰብሰቡ። (አንድ ላይ ብሉ) የአላህንም ስም በምግባቹ ላይ አውሱ። አላህ ምግባችሁን ይባርክላችኋል።"»

[ሐሰን ነው።] [አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

የተወሰኑ ሶሓቦች ነቢዩን - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ በማለት ጠየቁ: "እኛ እንበላለን። ነገር ግን አንጠግብም።" ነቢዩም - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለነርሱ እንዲህ አሏቸው: "ምን አልባት ስትበሉ ተበታትናችሁ ለየብቻ ነው እንዴ የምትበሉት?" እነርሱም: "አዎን" አሉ። እርሳቸውም: "ተሰብሰቡ ሳትበታተኑ ብሉ። ስትበሉ ቢስሚላህ በማለት የአላህን ስም አውሱ። በዛም ይባረክላችኋልም ትጠግባላችሁም።" አሏቸው።

فوائد الحديث

አብሮ ተሰባስቦ መብላትና ሲበሉ ቢስሚላህ ማለት ምግቡ በረከት እንዲኖረውና ለመጥገብ ምክንያት ናቸው።

መበታተን ባጠቃላይ መጥፎ ሲሆን መሰባሰብ በጠቃላይ ደግሞ መልካም ነው።

በመሰባሰብ ላይና ሲበሉ ቢስሚላህ በማለት ላይ መነሳሳቱን እንመለከታለን።

ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "በመሰባሰብ ቀለቦች ላይ በረከት ይወርዳል። የአላህን ስም በማውሳት ደግሞ የሸይጧንን ወደ ምግቡ መድረስ ያቅባል።"

التصنيفات

የመብላትና የመጠጣት ስነ-ስርዓት