አላህ ከርሱ የከለከለውን ይህን ቆሻሻ ድርጊት ራቁ። ይህን ድርጊት ከፈፀመም አላህ (ወንጀሉን) እንደሸሸገለት ይሸሽገው፤ ወደ አላህም ይመለስ። ወንጀሉን ለኛ ግልፅ የሚያደርግ ሰውም…

አላህ ከርሱ የከለከለውን ይህን ቆሻሻ ድርጊት ራቁ። ይህን ድርጊት ከፈፀመም አላህ (ወንጀሉን) እንደሸሸገለት ይሸሽገው፤ ወደ አላህም ይመለስ። ወንጀሉን ለኛ ግልፅ የሚያደርግ ሰውም በአላህ መጽሐፍ መሰረት (ቅጣቱን) እንፈፅምበታለን።

ከዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የአስለሚዩን ሰውዬ በድንጋይ ወግረው ከገደሉ በኋላ ተነስተው እንዲህ አሉ: "አላህ ከርሱ የከለከለውን ይህን ቆሻሻ ድርጊት ራቁ። ይህን ድርጊት ከፈፀመም አላህ (ወንጀሉን) እንደሸሸገለት ይሸሽገው፤ ወደ አላህም ይመለስ። ወንጀሉን ለኛ ግልፅ የሚያደርግ ሰውም በአላህ መጽሐፍ መሰረት (ቅጣቱን) እንፈፅምበታለን።"

[ሶሒሕ ነው።] [Al-Bayhaqi - Al-Haakim]

الشرح

ኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ማዒዝ ቢን ማሊክ አልአስለሚይን ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በዝሙት ቅጣት በድንጋይ ወግረው ከገደሉት በኋላ ተነሱና ለሰዎች ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ: አላህ የከለከላቸው የሆኑትን እነዚህን ቆሻሻ፣ ፀያፍና አስቀያሚ ወንጀሎች ራቁ። ከነዚህ ወንጀሎች አንዳችን የፈፀመ ካለም ሁለት ነገር መፈፀም ይጠበቅበታል: የመጀመሪያው: አላህ ወንጀሉን እንደሸሸገለት ተሸሽጎ ወንጀሉን አለመናገር። ሁለተኛው: ወደ አላህ ተውበት በማድረግ መቻኮል፣ በርሱ ላይ አለመዘውተር ነው። ወንጀሉ ለኛ ግልፅ የሆነችበት ሰው በርሱ ላይ በአላህ መጽሐፍ መሰረት ለዚህች ወንጀሉ የተጠቀሰውን ቅጣት እንፈፅምበታለን።

فوائد الحديث

ወንጀለኛ የሆነ ሰው ነፍሱን በመሸሸግ ላይና በርሱና በጌታው መካከል ካሉ ወንጀሎች ተውበት በማድረግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

የሚያስቀጡ ወንጀሎች መሪ ዘንድ የደረሱ ጊዜ የግድ ቅጣቱን ተፈፃሚ ማድረግ እንዳለበት እንረዳለን።

ወንጀሎችን መራቅና ለወንጀሎች ተውበት ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

ተውበት