إعدادات العرض
አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ያሉት መብቶች ስድስት ናቸው።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምንድን ናቸው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ያገኘኸው ጊዜ ሰላምታን አቅርብለት፤ የጠራህ…
አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ያሉት መብቶች ስድስት ናቸው።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምንድን ናቸው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ያገኘኸው ጊዜ ሰላምታን አቅርብለት፤ የጠራህ ጊዜ ጥሪውን አክብር፤ ካንተ ምክርን በፈለገ ጊዜ ምከረው፤ አስነጥሶ አላህን ያመሰገነ ጊዜ "የርሐሙከሏህ" በለው፤ የታመመ ጊዜ ጠይቀው፤ የሞተም ጊዜ ቅበረው።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: «"አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ያሉት መብቶች ስድስት ናቸው።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምንድን ናቸው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ያገኘኸው ጊዜ ሰላምታን አቅርብለት፤ የጠራህ ጊዜ ጥሪውን አክብር፤ ካንተ ምክርን በፈለገ ጊዜ ምከረው፤ አስነጥሶ አላህን ያመሰገነ ጊዜ "የርሐሙከሏህ" በለው፤ የታመመ ጊዜ ጠይቀው፤ የሞተም ጊዜ ቅበረው።"»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Kiswahili অসমীয়া Tiếng Việt ગુજરાતી Nederlands മലയാളം Română ไทยالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ወንድሙ ላይ ካሉት ሐቆች መካከል ስድስቱን ጠቀሱ፡ የመጀመሪያው: ባገኘው ጊዜ "አስሰላሙ ዐለይኩም" (ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን) በማለት ሰላምታውን ያቅርብለት። እርሱም "ወዐለይኩሙ-ስሰላም" በማለት ሰላምታውን ይመልስለት። ሁለተኛው: ለሰርግና ለሌሎች ድግሶች በጠራው ጊዜ ጥሪውን ማክበር ነው። ሶስተኛው: ምክር ባስፈለገው ጊዜ ያለምንም ማሞኘትና ማታለል መምከር ነው። አራተኛው: አስነጥሶ "አልሐምዱሊላህ" (ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባው ነው) ያለ ጊዜ "የርሐሙከላህ" (አላህ ይዘንልህ፤ ይቅር ይበልህ) በማለት አስደስተው። እርሱም "የህዲኩሙሏህ ወዩስሊሕ ባለኩም" (አላህ ይምራህ፤ ጉዳይህንም ያስተካክልልህ) በማለት ይመልስ። አምስተኛው: በታመመ ጊዜ ይጠይቀው፤ ይጎብኘው። ስድስተኛው: በሞተ ጊዜ ይስገድበት፤ እስኪቀበር ድረስም ጀናዛውን ይከተለው።فوائد الحديث
ሸውካኒይ እንዲህ ብለዋል: "(የሙስሊም ሐቅ) በማለት የተፈለገው መተዉ የማይገባ ማለት ነው። ይህንንም መፈፀም ወይ በግዴታ መልኩ ይሆናል፤ ወይም መተዉ በማይገባ ልክ አጽንዖት የተሰጠውና ግዴታን የሚመስል ተወዳጅ (መንዱብ) በሆነ መልኩ ይሆናል።
ሰላምታን መመለስ ሰላምታ የቀረበለት ሰው አንድ ሰው ከሆነ የነፍስ ወከፍ ግዴታ ይሆናል። በብዛት ለሆኑ ሰዎች ከሆነ ግን ስለ ሁሉም ሰላምታውን አንዱ ቢመልስ ራሱ በቂ ነው። ሰላምታን መጀመር ግን ከመሰረቱ ሱና ነው።
የታመመን መዘየር አንድ ሙስሊም በሙስሊም ወንድሞቹ ላይ ካሉት ሐቆች መካከል አንዱ ነው። ምክንያቱም ህመምተኛን መዘየር ቀልቡ ውስጥ ደስታና መፅናናትን ስለሚያመጣ ነው። ፈርዱ ኪፋያ (የተወሰኑ ሰዎች ከፈፀሙት በቂ የሚሆን) ግዴታም ናት።
ወንጀል እስካልሆነ ድረስ ጥሪን ማክበር ግዴታ ነው። ጥሪው ለሰርግ ድግስ ከሆነ አብዛኛው ዑለማዎች ሸሪዓዊ ምክንያት ኖሮት ካልቀረ በቀር ጥሪ ማክበሩ ግዴታ ነው ብለዋል። ከሰርግ ውጪ ለሆነ ጥሪ ከሆነ ግን አብዛኛው ዑለማዎች ጥሪ ማክበሩ ተወዳጅ (ሙስተሓብ) ነው ብለዋል።
አስነጣሹ አላህን ሲያመሰግን የሰማ ሰው አስነጣሹን "የርሐሙከሏህ" ማለቱ ግዴታ ነው።
የሸሪዓ ምሉዕነትና የማህበረሰቡን አንድነት፣ ኢማናቸውንና የውዴታቸውን ግንኙነት በመካከላቸው ለማስተሳሰር መጣሩን እንረዳለን።
(ፈሰምሚትሁ) የሚለው ዘገባም መጥቷል። በአንዳንዱ ደግሞ (ፈሸምሚትሁ) በሚል ተዘግቧል። ትርጉሙም በመልካምና በበረከት ዱዓ ማድረግ ነው። "ተሽሚት" ማለት አላህ የጠላት መደሰቻ ከመሆን ያርቅህ፤ ጠላትህን ከሚያስደስት ነገር ያርቅህ ማለት ነው። "ተስሚት" ማለት ደግሞ አላህ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይምራህ ማለት ነው።