إعدادات العرض
የሙስሊም ሽርጥ እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ ነው። ከባቱ ግማሽና በቁርጭምጭሚቱ መሃል ቢሆንም ግን ችግር የለውም። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ያለ ከሆነ እርሱ እሳት ውስጥ ነው። ሽርጡን በኩራት…
የሙስሊም ሽርጥ እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ ነው። ከባቱ ግማሽና በቁርጭምጭሚቱ መሃል ቢሆንም ግን ችግር የለውም። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ያለ ከሆነ እርሱ እሳት ውስጥ ነው። ሽርጡን በኩራት የጎተተን ሰው አላህ ወደርሱ አይመለከትም።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "የሙስሊም ሽርጥ እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ ነው። ከባቱ ግማሽና በቁርጭምጭሚቱ መሃል ቢሆንም ግን ችግር የለውም። ከቁርጭምጭሚት ዝቅ ያለ ከሆነ እርሱ እሳት ውስጥ ነው። ሽርጡን በኩራት የጎተተን ሰው አላህ ወደርሱ አይመለከትም።"
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Português සිංහල Tiếng Việt অসমীয়া Nederlands Kiswahiliالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ወንድ ሙስሊም ሽርጡን ምን ማድረግ እንዳለበት ገለፁ። ሽርጥ ሲባል (በዚህ አገባቡ) የወንድን ከወገብ በታች የሚሸፍን የሆነ ልብስ ሁሉ የሚመለከት ነው። ይህም ሶስት ሁኔታዎች አሉት: የመጀመሪያው: ተወዳጅ የሆነ ነው። ይህም እስከ ባቱ ግማሽ ድረስ አሳጥሮ ማድረግ ነው። ሁለተኛው: ሳይጠላ የሚፈቀድ ነው። ይህም ከባቱ ግማሽ በታች እስከ ቁርጭምጭሚቱ ድረስ ባለው አሳጥሮ ማድረጉ ነው። ቁርጭምጭሚት ማለት በባትና እግር መካከል የሚለየው እብጥ ያሉት አጥንቶች ናቸው። ሶስተኛው: ክልክል የሆነው ነው። ይህም ከቁርጭምጭሚት በታች መሆኑ ነው። ይህም እሳት እንዳያገኘው ይፈራለታል። ከቁርጭምጭሚቱ በታች ያስረዘመው በኩራት፣ በመመፃደቅና በጥመት ከሆነ ደግሞ አላህ ወደርሱ አይመለከትም።فوائد الحديث
ይህ ባህሪና ዛቻ በወንዶች ላይ ብቻ የተገደበ ነው። ሴቶች እዚህ ውስጥ አይካተቱም። ምክንያቱም እነርሱ ሰውነታቸውን ባጠቃላይ እንዲሸፍኑ የታዘዙ ስለሆኑ ነው።
የወንድን ከወገብ በታች የሚሸፍን የሆነ ልብስ ሁሉ "ኢዛር" ተብሎ ይጠራል። እንደሱሪና ሌሎች ልብሶች ይመስል። እነዚህ ሁሉ ልብሶች እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሰው ሸሪዓዊ ህግጋት ውስጥ ይገባሉ።
التصنيفات
የአለባበስ ስነ-ስርዓት