በኔ ላይ ጀነትና እሳት ቀረቡ። እንደዛሬ መልካምና መጥፎ ነገር ተመልክቼ አላውቅም። እኔ የማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ትንሽ ስቃቹ ብዙ ታለቅሱ ነበር።

በኔ ላይ ጀነትና እሳት ቀረቡ። እንደዛሬ መልካምና መጥፎ ነገር ተመልክቼ አላውቅም። እኔ የማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ትንሽ ስቃቹ ብዙ ታለቅሱ ነበር።

ከአነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ከባልደረቦቻቸው አንድ ጉዳይ ደረሳቸውና ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ: "በኔ ላይ ጀነትና እሳት ቀረቡ። እንደዛሬ መልካምና መጥፎ ነገር ተመልክቼ አላውቅም። እኔ የማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ትንሽ ስቃቹ ብዙ ታለቅሱ ነበር።"» አነስ እንዲህ አለ: "በአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሶሓቦች ላይ ከዚህ ቀን የበለጠ ከባድ ቀን መጥቶ አያውቅም።" አነስ እንዲህም አለ: «ሶሓቦች ጭንቅላታቸውን ሸፍነው እየተንሰቀሰቁ አለቀሱ። ዑመርም ተነሳና እንዲህ አለ: "በአላህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት ወደድን።" ያ ሰውዬም ተነሳና እንዲህ አለ: "አባቴ ማን ነው?" እርሳቸውም "አባትህ እገሌ ነው።" አሉት። በዚህም ጊዜ ይህቺ አንቀፅ ወረደች {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለፁ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ።} [አልማኢዳህ:101]»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ከባልደረቦቻቸው አንድ ጉዳይ ደረሳቸው። እርሱም እነርሱ ለርሳቸው ጥያቄ እያበዙ መሆናቸው ነው። የዛኔም ተቆጥተው ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ: "በኔ ላይ ጀነትና እሳት ቀረቡ። ዛሬ ጀነት ውስጥ ካየሁት መልካም ነገር የበለጠ መልካም ነገር አይቼ አላውቅም። ዛሬ እሳት ውስጥ ካየሁት መጥፎ ነገር የበለጠም መጥፎ ነገር አይቼ አላውቅም። እኔ ያየሁትን ብታዩ፣ ዛሬና ከዛሬ በፊት ከተመለከትኩት ያወቅኩትንም ብታውቁ ኖሮ እጅግ ከፍተኛ ፍርሃትን ትፈሩ ነበር። ሳቃችሁ አንሶ ለቅሷችሁም ይበዛ ነበር።" አነስም ረዲየሏሁ ዓንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አለ: "በአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሓቦች ላይ ከዚህ ቀን የበለጠ ከባድ ቀን መጥቶ አያውቅም። ጭንቅላታቸውን ሸፍነው እጅግ ከማልቀሳቸው የተነሳ ለቅሷቸው ከአፍንጫ የሚወጣ የመንሰቅሰቅ ድምፅ ነበረው።" ዑመርም ረዲየሏሁ ዓንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ተነስተው እንዲህ አሉ: "በአላህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነትና በሙሐመድ ነቢይነት ወደድን።" አነስ እንዲህ አለ: ያ ሰውዬም ተነሳና እንዲህ አለ: "አባቴ ማን ነው?" እርሳቸውም "አባትህ እከሌ ነው።" አሉ። በዚህን ጊዜም ይህቺ አንቀፅ ወረደች: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለፁ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ።} [አልማኢዳህ:101]

فوائد الحديث

የአላህን ቅጣት በመፍራት ማልቀስና ሳቅ አለማብዛት እንደሚወደድ እንረዳለን። ሳቅ ማብዛት ዝንጉነትንና የቀልብ ድርቀትን የሚጠቁም ነውና።

ሶሓቦች ረዺየሏሁ ዐንሁም - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ምክር ተፅእኖ የሚያሳድርባቸውና የአላህን ቅጣት አጥብቀው የሚፈሩ መሆናቸውን እንረዳለን።

በማልቀስ ወቅት ፊትን መሸፈን እንደሚወደድ እንረዳለን።

ኸጧቢይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የሚመለከተው የማያስፈልገው የሆነን ነገር ተጨንቆ ወይም ለማሳሳት የሚጠይቅን ነው። አንዳች ጉዳይ ስለገጠመው የግድ አስፈልጎት የሚጠይቅ ግን ወንጀልም ሆነ ወቀሳ የለበትም።"

አላህን በመገዛት ላይ፣ ፅናት በማድረግ ላይ፣ አላህን ከመወንጀል በመራቅ ላይና የአላህ ድንበርን ሳይተላለፉ በመቆም ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

ይህ ሐዲሥ በምክርና በማስተማር ወቅት መቆጣት እንደሚፈቀድ እንረዳለን።

التصنيفات

የጀነትና እሳት ባህሪዎች