إعدادات العرض
ሸይጧን የአላህ ስም እንዳይወሳበት በማድረግ ምግቡን ለራሱ የተመቸ ያደርገዋል።
ሸይጧን የአላህ ስም እንዳይወሳበት በማድረግ ምግቡን ለራሱ የተመቸ ያደርገዋል።
ከሑዘይፋ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ማዕድ ለመጋራት የተገኘን ጊዜ የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጃቸውን ወደ ማዕዱ ከመስደዳቸውና (ከመጀመራቸው) በፊት እኛ እጃችንን አንሰድም ነበር። አንድ ቀን ከርሳቸው ጋር ማዕድ ለመጋራት ተገኘን። (ከፍጥነቷ የተነሳ) ልክ እየተገፈተረች በሚመስል መልኩ የሆነች አንዲት ልጅ መጣችና እጇን ወደ ማዕዱ ሰደደች። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጇን ያዟት። ቀጥሎም (ከፍጥነቱ የተነሳ) ልክ እየተገፈተረ በሚመስል መልኩ አንድ የገጠር ሰውዬ መጣና እጁን ወደ ማዕዱ ሰደደ። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እሱንም እጁን ያዙትና እንዲህ አሉ: "ሸይጧን የአላህ ስም እንዳይወሳበት በማድረግ ምግቡን ለራሱ የተመቸ ያደርገዋል። እርሱም ይህቺን ሴትዮ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዞ መጣ። እጇንም ያዝኳት። ይህንንም ሰውዬ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዞ መጣ። እጁንም ያዝኩት። ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! የሸይጧንን እጅ ከሴትዮዋ እጅ ጋር ይዤዋለሁ።"»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ሑዘይፋ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት: ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ማዕድ ለመጋራት በተገኙ ጊዜ የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጃቸውን ወደ ማዕዱ ከመስደዳቸውና ከመጀመራቸው በፊት እነርሱ እጃጀውን አይሰዱም ነበር። አንድ ቀን ከርሳቸው ጋር ማዕድ ለመጋራት ተገኘን። ከፍጥነቷ የተነሳ አመጣጧ ልክ እየተገፈተረች በሚመስል መልኩ የሆነች አንዲት ሴትዮ መጣችና እጇን ወደ ማዕዱ ሰደደች። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጇን ያዟት። ቀጥሎም ከፍጥነቱ የተነሳ አመጣጡ ልክ እየተገፈተረ በሚመስል መልኩ የሆነ አንድ የገጠር ሰውዬ መጣና እጁን ወደ ማዕዱ ሰደደ። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ምግቡን ከመንካቱ በፊት እጁን ያዙትና እንዲህ አሉ: "ሰውዬው የአላህ ስም ሳይወሳበት ምግቡን የጀመረ ጊዜ ሸይጧን ምግቡን ለመመገብ ይመቻቻል። እርሱም ይህቺን ሴትዮ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዟት መጣ። እጇንም ያዝኳት። ይህንንም ሰውዬ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዞት መጣ። እጁንም ያዝኩት። ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! የሸይጧንን እጅ ከሴትዮዋ እጅ ጋር በእጄ ነው።" ካሉ በኋላ የአላህን ስም ካወሱ በኋላ ተመገቡ።فوائد الحديث
ሶሓቦች ለአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የነበራቸውን ክብርና ከርሳቸው ጋር የነበራቸውን ስነ ስርዓት እንረዳለን።
ከምግብ ስነ-ስርዓቶች መካከል ልጆች ትላልቆችና የተከበሩ ሰዎች ምግቡን እስኪጀምሩ ድረስ መጠበቃቸው ነው።
ሸይጧን ፍላጎቱን ለማሳካት እንዲመቸው አንዳንድ ዝንጉ የሆኑ ሰዎችን ለሚያስደስተው ተግባራት እንደሚልክ እንረዳለን። ከነዚህም ውስጥ እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የተጠቀሰው ይገኛል።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «ዑለማዎች እንዲህ ብለዋል: "ቢስሚላህ ሲሉ ሌላው እንዲሰማና እንዲያስታውስ ጮክ ብሎ ማለቱ ይወደዳል።"»
አንድ ሰው መብላት ፈልጎ ቢመጣና ቢስሚላህ ማለቱን ካልሰማህ ቢስሚላህ እስኪል ድረስ እጁን ያዘው።
አዋቂ የሆነ ሰው ውግዝ ተግባርን ማስተካከል ግዴታው ነው። አቅም ላለው ሰው ደግሞ ውግዝ ተግባርን በእጁ ማቀብ ግዴታው ነው።
ይህ ሐዲሥ ከአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ተዓምራት መካከል አንዱ ተዓምር ነው። ይኸውም አላህ በዚህ ታሪክ ውስጥ የተከሰተውን ለርሳቸው ማሳወቁ ነው።
ሸይጧን የአላህ ስም ባልተጠራበት ወቅት ካልሆነ በቀር የኢማን ሰዎችን ምግብ ለመመገብ አይቻለውም።
ሰዎችን ኢስላማዊ የአመጋገብና የአጠጣጥ ስነ-ስርዓት ማስተማር ይወደዳል።
ሰሚው ዘንድ ጉዳዩን አፅንዖት ለመስጠት መማል እንደሚወደድ እንረዳለን።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ውሃ፣ ወተት፣ ማር፣ መረቅ፣ መድሃኒትና ሌሎችንም መጠጦች በሚጠጣበት ወቅት ቢስሚላህ ማለት ልክ ምግብ ላይ ቢስሚላህ እንደማለት ነው።"
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «ሆን ብሎም ይሁን ረስቶ ወይም ባለማወቅ ወይም ተገዶ ወይም ድንገት ባጋጠመው ሰበብ ተስኖት ምግቡን ሲጀምር ቢስሚላህ ማለትን ቢተውና ከዚያም መሃል ላይ ማለት ቢመቸው ቢስሚላህ ማለቱ ይወደድለታል። የሚለውም "ቢስሚላሂ አወለሁ ወአኺረህ" ነው። ይህም ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ስላሉ ነው: "አንዳችሁ በሚመገብበት ወቅት የአላህን ስም ያውሳ። ሲጀምር የአላህን ስም ማውሳት ከረሳ ቢስሚላሂ አወለሁ ወአኺረሁ ይበል።" አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።»
التصنيفات
የመብላትና የመጠጣት ስነ-ስርዓት