إعدادات العرض
የአደም ልጅ ሁለት በገንዘብ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ ሶስተኛ ሸለቆ ይመኛል።
የአደም ልጅ ሁለት በገንዘብ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ ሶስተኛ ሸለቆ ይመኛል።
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "የአደም ልጅ ሁለት በገንዘብ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ ሶስተኛ ሸለቆ ይመኛል። የአደምን ልጅ ሆድ ከአፈር በቀር የሚሞላው የለም። ወደ አላህ ተፀፅቶ በተመለሰ ሰው ላይም አላህ ተውበቱን ይቀበለዋል።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français Kurdî Русский Tiếng Việt Magyar ქართული Kiswahili සිංහල Română অসমীয়া ไทย Hausa Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - የአደም ልጅ በወርቅ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ በተፈጥሮው ካለው ስግብግብነት አንፃር ሌሎች ሁለት ሸለቆዎችን ይመኝ ነበር። የአደም ልጅ ሙቶ ከርሱ በቀብሩ አፈር ካልሞላ በቀር ለዱንያ ስግብግብ ከመሆን አይወገድም።فوائد الحديث
የሰው ልጅ ገንዘብንና ሌሎችንም ዱንያዊ መጣቀሚያ በማግበስበስ ላይ ያለውን ከፍተኛ ጉጉት ያስረዳናል።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ ለዱንያ መጓጓት፣ ዱንያን ማብዛትና እርሷን መከጀል የተወገዘ መሆኑን እንረዳለን።"
አላህ ከተወገዘ ባህሪ ተፀፅቶ የሚመለስን ሰው ተውበት ይቀበላል።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የብዙሃኑን የአደም ልጆች የዱንያ ጉጉት ነው የገለፀው ይህንንም (ተፀፅቶ ተውበት ባደረገ ሰው ላይ አላህም ተውበቱን ይቀበለዋል።) የሚለው የነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና -ንግግር ያጠናክረዋል።"