ተራጋሚዎች የትንሳኤ ቀን መስካሪዎችም ሆነ አማላጅ አይሆኑም።

ተራጋሚዎች የትንሳኤ ቀን መስካሪዎችም ሆነ አማላጅ አይሆኑም።

ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ተራጋሚዎች የትንሳኤ ቀን መስካሪዎችም ሆነ አማላጅ አይሆኑም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላግባብ እርግማን የሚያበዛ ሰው ለሁለት ቅጣቶች እንደሚዳረግ ተናገሩ: የመጀመሪያው: የትንሳኤ ቀን መልክተኞች ለህዝቦቻቸው ተልእኳቸውን እንዳደረሱ ከሚመሰክሩ ምስክሮች አይሆኑም፤ አመፀኛ ስለሆነም በዱንያም ምስክርነቱ ተቀባይነት አይኖረውም፤ ሰማዕትነትንም እርሱም በአላህ መንገድ መገደል ስለሆነ አይገጠምም። ሁለተኛው: አማኞች የትንሳኤ ቀን እሳት መግባት ግድ የሆነባቸውን ወንድሞቻቸውን በሚያማልዱበት ጊዜ እነርሱ ግን አያማልዱም።

فوائد الحديث

መራገም ክልክል መሆኑንና ማብዛቱ ደግሞ ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብ መሆኑን እንረዳለን።

ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰው ቅጣት ለአንዴና ለመሳሰሉት ለተራገመ ሳይሆን እርግማን ለሚያበዛ ሰው ነው። በተጨማሪም የተፈቀደውን እርግማን የተራገመም ቅጣቱ አይመለከተውም። ይህም የተወገዘ ማንነት የተላበሱ ሰዎችን በጥቅል ማንነታቸው ግለሰብን ሳይነጥሉ መራገም በሸሪዓ የተፈቀደ ነው። "የአላህ እርግማን በአይሁድና በክርስቲያኖችን ላይ ይሁን" ፤ "በበዳዮች የአላህ እርግማን ይስፈን።" ፤ "ሰዓሊዎችን አላህ ይርገማቸው።" ፤ "የሉጥ ህዝቦችን ስራ የሰራ ሰው አላህ ይርገመው።" ፤ "ከአላህ ውጪ ላለ አካል ያረደ ሰው የአላህ እርግማን ይውረድበት።" ፤ "ወንድ ሆነው ከሴት ጋር የሚመሳሰሉ ሴት ሆነው ደግሞ ከወንድ ጋር የሚመሳሰሉ ሰዎችን አላህ ይርገማቸው።" ማለትህና የመሳሰሉትን በሸሪዓ መረገማቸው የተጠቀሱ አካላቶችን መራገም ይቻላል።

የትንሳኤ ቀን አማኞች እንደሚያማልዱ መጠቀሱን እንረዳለን።

التصنيفات

ውግዝ ስነ-ምግባር